የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ በአምስት የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች ላይ የካሪኩለም ክለሳ ውጫዊ ግምገማ አካሄደ

የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ በአምስት የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች ላይ የካሪኩለም ክለሳ ውጫዊ ግምገማ አካሄደ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ 5 ፕሮግራሞች ላይ ከዚህ በፊት በ3 ዓመት የሚያልቀውን በአዲሱ ፊኖተ ካርታ መሠረት በ4 ዓመት የሚጠናቀቅ ተደርጎ የተሠራውን ከመጀመሩ አስቀድሞ መገምገም ስላለበት ውጫዊ ግምገማ አካሂዷል።በግብርናና በደን ጥናት፣ በቱሪዝም ምህዳርና ባህል ቅርስ አስተዳደር፣ በደን አጠቃቀምና አስተዳደር፣ አጠቃላይ ደን አጠባበቅ፣ የዱር ህይወት ጥበቃ አስተዳደር ዙሪያ የመጀመርያ ድግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች ላይ ውጪያዊ ግምገማ ባደረገበት ወቅት ከፌዴራል፣ ከክልል እና ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች ሆነዋል።

የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ሞቱማ ቶሌራ በቦታው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት ኮሌጁ ለ43 ዓመታት በደንና ተፈጥሮ ሀብት ዙሪያ በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት የተጣለበትን ሀገራዊ ሀላፊነት እየተወጣ መቆየቱን አውስተው በሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ መሰረት የመጀመሪያ ድግሪ ፕሮግራሞችን ሀርሞናይዝድ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኢ/ር ፍሰሀ ጌታቸው በበኩላቸው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የዛሬውን ቅርጽ እና ስያሜ ከመያዙ በፊት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር በመሆን 200 ተማሪዎችን ተቀብሎ 30 በሚሆኑ መምህራን በአራት የትምህርት ፕሮግራሞች ብቻ የመማር ማስተማሩን ስራ መጀመሩን አስታውሰው ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ጊዜ ከ40 ሺህ በላይ ተማሪዎች፣ ከ2100 በላይ መምህራን እና 256 ከ1ኛ እስከ 3ኛ ድግሪ ያሉ የትምህርት ፕሮግራሞችን በውስጡ ይዞ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

በመጨረሻም የኮሌጁ የአካዳሚክ ጉዳዮች ተባባሪ ዲን የሆኑት አቶ ግርማ መኩሪያ ይህ ውጫዊ ግምገማም ቀደም ባሉት ጊዜያት እንደሚደረገው ሁሉ አዳዲስ የትምህርት ፕሮግራሞች ወደ ትግበራ ከመግባታቸው በፊት የሚካሄድ የግብአት መሰብሰቢያ ግምገማ በመሆኑ በርካታ ጠቃሚ ሀሳቦች ይገኛሉ የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et