የኢትዮጵያ ቱሪዝም ደርጅት ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር አዲሱን ምድረ ቀደምት (Ethiopia Land of Origins) የተሰኘዉን የቱረዝም መዳራሻ ብራንድ ዘርፉ ለሚመለከታቸዉ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መደርክ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናዉ ግቢ አካሂዷል፡፡
በመደርኩ ላይ የአምስት ክልሎች ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ባለሞያዎችና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት ት/ቤት ተመራቂ ተማሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡
መድረኩ አዲሱን የኢትዮጵያ የቱሪዝም ብራንድ ለባለደርሻ አካላት ከማስተዋወቅም ባሻገር ክልሎች የየራሳቸዉን የቱሪዝም መዳረሻ ብራንድ እንዲመሰርቱ የሚያግዝና ተማሪዎችም ወደ ስራ ዓለም በሚገቡበት ወቅት ብራንዱን እንዲረዱና እንዲተገብሩ የሚያስችል ነዉ፡፡ ይህንን ዓላማ ለማሳካት ስለ አዲሱ ብራንድ የቱሪዝም ኢትዮጵያ የማርኬቲንግ ኃላፊ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በዋናነት ምድረ ቀደምት የሚሰኘዉ አዲሱ ብራንድ ኢትዮጵያ የቡና፣ የሰዉ ዘር፣ የፍልስና፣ የሙዚቃ፣ የዘመናዊ ዴሞክራሲ፣ የምግብ አዝዕርት (Primary Plant domestication) እና የኃይማኖት መገኛ በመሆኗ እና ይህንን እንደ ብራንድ መጠቀም በቀላሉ ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ ያግዛል ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከምክክር መድረኩ ጋር የሚያያዝ የደቡብ ኢትዮጵያ የቱሪስት ሩት የመዳረሻ ግብይት ላይ የተሰራ ጥናታዊ ጸሑፍም ቀርቧል፡፡ በአጠቃላይ መደረኩ የታለመለትን ዓላማ ከግብ ያደረሰ ሲሆን ቱሪዝም ኢትዮጵያ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሮግራሙን ለማስተናገድ ያሳየዉን ፍላጎትና ተነሳሽነት አድንቋል፡፡ መሰል መድረኮችም በትብብር የሚሰራ እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን በጋራ ለመስራት የሚያስችል ምክክር እንደሚደረግ ታቅዷል።