የስነምግባርና ጸረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር አካሄደ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት የፌደራል የስነ-ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የተመሰረተበትን 20 ዓመት ምክንያት በማድረግ ለተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር አዘጋጅቷል፡፡

በሚያዚያ 19 ቀን 2013 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ ከሰባቱም ካምፓሶች የጥያቄና መልስ ውድድር በማድረግ አብላጫ ውጤት ላመጡት ተወዳዳሪ ተማሪዎች  በዩኒቨርሲቲው ደረጃ የአሸናፊዎች አሸናፊ የተለየ ሲሆን ለአሸናፊዎቹም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

አቶ አየለ አደቶ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ በዕለቱ ተገኝተው በአሁኑ ሰዓት በሃገራችን የስነምግባር ጥያቄ አንገብጋቢ፣ አሳሳቢ፣ በጣም አስፈላጊና ቀጣዩስ ትውልድ ምን ይጠብቀዋል በምንልበት ወቅት የስነ ምግባር ጉዳይ ይመለከተኛል ብላችሁ ይህን ፕሮግራም ያዘጋጃችሁና የተገኛችሁ በተለይ ደግሞ የዕለቱ ተወዳዳሪ ተማሪዎች ታላቅ ምስጋና ይገባችኃል ብለዋል፡፡ ኃላፊው  አክለውም እንደተናገሩት የዛሬው ተወዳዳሪዎችም ስነምግባራቸውን በማስቀጠል በአሸናፊነት እና በእችላለሁ መንፈስ በዩኒቨርሲቲያችን ብቻ ሳይሆን በሀገር አቀፍ ደረጃም አሸናፊ በመሆን የሚያጋጥሟችሁን በርካታ ሰንካላ አስተሳሰቦች እና አመለካከቶችን በመቋቋምና በመወጣት ፍቅርን፣ ሰላምን እና አንድነትን በመስበክ የበኩላችሁን እንድትወጡ አደራ እላለሁ ብለዋል፡፡

የስነ-ምግባርና  ጸረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ከበደ ኩማ እንደገለጹት ተማሪዎች  ከብሄርተኝነትና ከኃይማኖት ጽንፈኝነት የጸዳ አስተሳሰብ በመያዝ፣እርስ በእርስ ሰላማዊ ግንኙነት በመፍጠር፣ በመቻቻል መንፈስና የተቋሙን ህግና ደንብ በማክበር ለሰላም ተቆርቋሪ መሆን ይኖርባችኃል ብለዋል፡፡

በዕለቱም ከሴቶች ተማሪ አምላክ ስዩም ከዋናው ግቢ እንዲሁም ተማሪ ባህሩ ዘውዴ ከወንዶ ገነት ኮሌጅ አሸናፊ በመሆን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲን የሚወክሉ መሆኑ ተገልጾ ለተወዳዳሪዎችም የምስክር ወረቀት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et