ለተቋሙ ሠራተኞች ግንዛቤ ለማስጨበጥ በወንዶ ገነት ደ/ተ/ሀ/ኮሌጅ የካቲት 4 ቀን 2013 ዓ.ም የተዘጋጀው ስልጠና በተጀመረበት ወቅት በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንትፊክ

ዳይሬክተር ዶ/ር ፋሲካ ቤተ በተማሪዎች ላይ ስንሠራ፣ ምርምር ስናደርግ እና የማህበረሰብ አገልግሎት ስንሰጥ በዕቅድ መመራት ግድ ይለናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ካልታቀደ ምንም ቢሠራ ውጤት አይኖርም ያሉት ዳይሬክተሩ ባልታቀደ የትምህርት አሰጣጥ ተማሪዎችን ማበላሸቱ ሀገርን ከማበላሸት አልፎ ማፍረስ መሆኑን በመገንዘብ በዘመነ የዕቅድ አዘገጃጀትና ሪፖርት አቀራረብ ክንውኖቻችንን ማሳለጥ እንደሚገባ አስምረውበታል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የፕላንና ተቋማዊ ለውጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ቡርቃ በበኩላቸው ዕቅድ አዘገጃጀቱ በተሻሻለ መንገድ የቀረበ መሆኑን ገልጸው የትኩረት መስኮችን በመለየት፣ ዕይታዎችንና ግቦችን በማቀናጀትና ውጤታማ የሆነ ዕቅድ በማቀድ በመጨረሻም አፈጻጸሙን በሚገባ የሚያሳይ ሪፖርት አዘጋጅቶ ማቅረብ በየደረጃው ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ ግንባር ቀደም ተግባር ነው ብለዋል፡፡ አክለውም ከዚህ ጋር ተያይዞ ጥራቱንና ወቅታዊነቱን የጠበቀ መረጃ ፍሰት በየተቋሙ እንዲኖር ሁላችንም የበኩላችንን መወጣት ይገባናል ሲሉ አጠቃለዋል፡፡

ስልጠናውን በመሳተፍ ላይ የሚገኙ የአስተዳደር ሠራተኞች፣ ዳይሬክተሮች፣ የቡድን መሪዎች እና የት/ክፍል ሀላፊዎች በየሥራ ክፍላቸው በተለያየ ቡድን በመከፋፈል የጠለቀ ውይይት ያካሄዱ ሲሆን በግብረ መልሱ ጽብረቃ ሰፊ ግንዛቤ ያሳደረ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ስልጠናውን በመለጠቅ የኢንስቲትዩቱ የፕላንና መረጃ ማኔጅመንት አስተባባሪ የሆኑት አቶ አስራት ማሙዬ የኢንስቲትዩቱን የ10 ዓመት ስትራቴጂክ መሪ ዕቅድ ያቀረቡ ሲሆን አስቀድሞ በተፈጠረው ግንዛቤ መነሻ የተሳካ ውይይት ተደርጎ ዶ/ር ፋሲካ ሲያጠቃልሉ ይህ በቀጣይነት እስከታችኛው ክፍል ወርዶ የተጧጧፈ ውይይት መካሄድ እንዳለበት በአጽንዖት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በማጠናቀቂያውም ላይ መድረኩን ያዘጋጀው የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን መድረኩ የታለመለትን ዓላማ ግብ መምታቱን ገልጸው ተሳታፊዎችንና ሌሎች ለዝግጅቱ አስተዋፅዖ ያደረጉትን አባላት በማመስገን ተሰብሳቢዎችን ሸኝተዋል፡፡  

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et