የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለሀዋሳ ክላስተር ዩኒቨርሲቲዎች፣ ለምርምር ተቋማት እና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በምርምር ስነ-ምግባር ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ከየካቲት 26-27/2013 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሰጥቷል፡፡

በመክፈቻ ንግግር ላይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትዶ/ር አያኖ በራሶ  ዩኒቨርሲቲዎችን በተኩረት መስክ እና በተልዕኮቻቸው የመለየት ጥናት በተደረገው መሰረት የምርምር ዩኒቨርሲቲ እንዲሆኑ ከሚጠበቁት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ዩኒቨርሲቲያችን አንዱ እንደመሆኑ በቀጣይ የምርምር  ዩኒቨርሲቲ ማሟላት ያለበትን መመዘኛ ለማሟላት በአስር ዓመቱ ዕቅዳችን ውስጥ የመጀመሪያ ድግሪ ፕሮግራሞችን በመቀነስ በሁለተኛ እና ሶስተኛ ድግሪ ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራት መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ችግር ፈቺ ምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ትኩረት በመስጠት በተለይም የአካባቢው ህብረተሰብ የግብርና ምርትና ምርታማነትን የሚያሻሽሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን የማስተዋወቅ፣ የማላመድና የማሰረጨት ተግባር እየተከናወነ ሲሆን የዚህ መሰሉ የምርምር ስነ-ምግባር ስልጠና በመማር ማስተማሩ የትምህርትን ጥራት ከማስጠበቅ እና  የምርምር ስራዎቻችን አለም አቀፋዊ እንዲሁም ችግር ፈቺ እንዲሆኑ ፋይዳው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚ/ዲኤታ ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት የምርምር ስነ-ምግባር ስልጠና ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ እንደተካሄደ እና ይሄኛውም ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን አስታውሰው ምርምር ትልቅ ስነ ምግባር የሚፈልግ ተግባር ሲሆን የምርምር ስነምግባር መርሆዎችን ተከትለው የሚሰሩ ምርምሮች ለሀገራችን ችግር ፈቺ ምርምሮችን ከማበርከታቸውም በተጨማሪ በሰው ልጆች፣ በዕጽዋቶች፣ በእንስሳት እና በአጠቃላይ  ስነምህዳር ላይ ችግሮች እንዳይከሰቱ በእጅጉ ይረዳናል ብለዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et