ዶ/ር ከበደ ተ/ሚካኤል፣ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብ ኮሌጅ ዲን ተወካይና የኮሌጁ ተባባሪ ዲን በፕሮገራሙ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር በፕሮግራሙ መከፈት እንደ ማህበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብ ኮሌጅ ደስተኛ መሆናቸዉን ከገለጹ በኋላ ት/
ክፍሉ ያለውን የሰው ኃይልን ተጠቅሞ የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት እና የምርምር ዘርፉን ለማሳደግ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ እና ቁርጠኝነት እንደ ሀገር የተያዘውን የምርምር ዘርፍ ዕድገት ለማሳካት ትልቅ አስተዋፅዖ እንዳለው ገልፀዋል::
የጂኦግራፊና አከባበቢ ት/ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ሙሉእመቤት ወርቁ በበኩላቸው ትምህርት ክፍሉ የትምህርት ስልጠናና የምርምር ዘርፉን ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሆነ ገለጸዋል:: አያይዘውም ባሁን ሰዓት በአራት የተለያዩ መስኮች ማለትም የውሀ ሀብትና የአየር ንብረት መቋቋም (Water Resource and Climate Change Adaptation)፣ የመሬት ሀብት አስተዳደር (Land Resource Management)፣ ክልላዊና በከተማ ልማት አስተቃቀድ (Regional and Urban Development Planning) እና ጂኦግራፊያዊ መረጃ ዘዴና የካርታ ዝግጅትና ትንተና (Geo-Spatial Planning and Digital Cartography) አዳዲስ ስርዓተ ትመህርት ተቀርጾ አስፈላጊውን ውስጣዊ ግምገማ (internal curriculum review) ሂደት ጨርሰን ወደ ስራ ከመገባቱ በፊት ለውጫዊ (external) የስርዓተ ትምህርት ግምገማ የቀረበ መሆኑን አመላክተዋል::