አማካሪዋ ወይዘሮ ማሪ ማርቲሰን (Marie Martisen) እና ቡድኑ ለሁለት ቀናት የሚቆየው ጉብኝታቸውን ባካሄዱበት ወቅት የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ሞቱማ ቶሌራ የMRV (National Measuring Reporting and verification)

ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶ/ር አብደላ ጉሬን ጨምሮ ሌሎች የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮች እና የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ መንግስት የRedd+ (Plus) ፕሮጀክት አስተባባሪው ዶ/ር ተሻለ ወ/ማርያም በስፍራው በመገኘት እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።

ቡድኑ የካቲት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ጉብኝቱን በMRV ፕሮጀክት ሥር የሚደገፉ የሁለተኛ ዲግሪ (MSc) ተማሪዎች የሚገለገሉበትን ላብራቶሪ በመመልከት የጀመረ እና በኢትዮጵያ ኖርዌይ ኢምባሲ የሚደገፍ ሆኖ ጅማሬውም እ.ኤ.አ ታህሳስ 2014 ዓ.ም ሲሆን የፕሮጀክቱ ማብቂያ እ.ኤ.አ ጥር 2021 ዓ.ም ቢሆንም ነገር ግን በኮቪድ-19 መከሰትና ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች የተነሳ የታለመለትን ዓላማ ባለማሳካቱ እስከ ነሐሴ 2021 ድረስ የተራዘመ እንደሆነ ታውቋል። በመቀጠልም በኮሌጁ የሚገኙትን ሌሎች ላብራቶሪዎች፣ቤተ-መፅሀፍቶችን እና የተለያዩ የፍራፍሬና የእጽዋት ምርምሮችን  ተመልክተዋል።

በዚሁ እለት ከሰዓት በኋላ ቀጥሎ በዋለው የቡድኑ ጉብኝት ኮሌጁ በሀገር ውስጥና ከሃገር ውጭ በስፋት የሚታወቅበትን ውብና ማራኪ የተፈጥሮ ደን ተዘዋውረው በተመለከቱበት ወቅት በእፅዋቶቹ ላይ ምርምር እያደረጉ ያሉ መምህራን ለጎብኚ ቡድኑ ሰፊ ማብራርያና ገለፃ አድርግዋል። በጉብኝታቸው ወቅት በአፄኃይለ ስላሴ ዘመን በኖርዌይ መንግስት Norad (The Norwagian Agency for Development Cooperation) ኤጀንሲ የተገነባውን ግድብ አሁናዊ ሁኔታ ከተመለከቱ በኋላ ባዩት ነገርና በተደረገላቸው ገለጻ መደሰታቸውን እና ኮሌጁ በምርምሩ ዘርፍ እያደረገ ያለውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን ነገሌ አርሲ ወረዳ ገበታ አርጃ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ የሚገኘውን የግራር ደን ሳይት ለመመልከት ተገኝተዋል። በወቅቱ ገለፃ ያደረጉት የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ሞቱማ ቶሌራ የምርምር ሳይቱ እ.ኤ.አ በ 2006 ዓ.ም በኮሌጁ በጀት የተጀመረ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ በሚዘወተረው እንጨቶችን ለማገዶነት የመጠቀም እና ከብቶችን ለግጦሽ ማሰማራት የተነሳ ደኑ ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን አክለዋል።በዚህም የተነሳ ኮሌጁ ደኑን አጥር ለማሳጠር ከኖርዌይ ኤምባሲጋር ስምምነት ቢፈፅምም በኮቪድ-19 እና ሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች ተጓትቶ ቆይቷል።ይሁን እንጂ ቡድኑ በጉብኝቱ ወቅት በጀቱን በቶሎ ለማስለቀቅና የአጥር ስራውን በፍጥነት ለማስጀመር ቃል ገብተዋል

በመጨረሻም በሻላ እና አቢጃታ ሀይቆች ብሔራዊ ፓርክ በመገኘት በአስጎብኚው የተደረገላቸውን ገለፃ ተከታትለዋል። ፓርኩ 887km² የሚሸፍን ሲሆን በውስጡም የተለያዩ የእንስሳት እና የአእዋፋት ዝርያዎችን ያቀፈ ሲሆን በፓርኩ በብዛት የሚገኙት የአእዋፋት አይነቶች የውሃ ላይ አእዋፋት መሆናቸውን እና የሻላ ሃይቅ በጥልቀቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ሃይቆች አንደኛ ስለመሆኑ እንዲሁም በቅርቡ የኢፊዲሪ  ጠ/ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ  የሻላ በአቢጃታ ሃይቆች ስጎበኙ በአቢጃታ ሃይቅ ላይ እየተጋረጡ ያሉትን ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለመከላከል መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት መናገራቸውን ለቡድኑ በአስጎብኚው ተገልጾላቸዋል።

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et