ኮሌጁ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጥራት ማረጋገጫና ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በቀን 01/06/2013 ዓ.ም ለት/ክፍል ሃላፊዎች እና የጥራት ማረጋገጫና ማሻሻያ አስተባባሪዎች ስልጠና በአዋዳ ካምፓስ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ 

በስልጠናው ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ወገኔ ማርቆስ በት/ክፍል አስተባባሪዎች መካካል ባለው ክፍተትና የተደራጀ የመስሪያ ሰነድ ያለመኖር የትምህርት ጥራቱን በተፈለገው ደረጃ ለማረጋገጥ ችግር ሆኖ መቆየቱንና ለዚህም አስፈላጊው ሰነድ የተዘጋጀበት ይህ ስልጠና ክፍተቱን ለመሙላት ትልቅ አቅም እንደሚሆን ገልጸው የት/ክፍል ሃላፊዎችና አስተባባሪዎች ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል፡፡

በስልጠናው ላይ የመግቢያ ንግግር ያደረጉት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጥራት ማረጋገጫና ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ መቅደስ መኮንን በበኩላቸው የትምህርት ጥራት የአንድ ወቅት ስራ አለመሆኑን አውስተው ለዚህም ኮሌጁ ተከታታይ ክትትል እንዲያደርግ በማሳሰብ የስራ ክፍላቸው አስፈላጊዉን ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡

ስልጠናው ሁለት መርሐግብሮችን ያካተተ ሲሆን በመጀመሪያ የት/ክፍል የጥራት ማረጋገጫና ማሻሻያ አስተባባሪዎች ሃላፊነትና ተግባር በተመለከተ በዶ/ር ቸሩ አጽመጊየርጊስ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጥራት ማረጋገጫና ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ተባባሪ ዳይሬክተር እና በማስከተልም የኮሌጁ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫና ማሻሻያ ሰነድ በረዳት ፕሮፌሰር አማረ ያዕቆብ የኮሌጁ የትምህርት ማረጋገጫና ማሻሻያ ሃላፊ ተሰጥቷል፡፡ በስልጠናው ከ20 በላይ ታዳሚዎች ተሳትፈዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et