የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከሀዋሳ ከተማ ትምህርት መምሪያ ጋር በመተባበር “ጤና ለአንድ ሴት ተማሪ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ስልጠና ከጥር 27 እስከ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ

ሰጥቷል፡፡ በዕለቱ በቦታው የተገኙት የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ረ/ፕሮፌሰር አለሙ ጣሚሶ የከተማችንን ሴት ተማሪዎች ለማብቃት እንዲሁም ተሳትፎአቸውንና ተጠቃሚነታቸውን በሁሉም ዘርፍ ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወኑ መሆናቸዉን ጠቅሰዉ ሴት ተማሪዎቻችን በትምህርታቸው ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ሕይወታቸውን በክህሎትና በጥበብ እንዲመሩ እየተሰራ  ይገኛል ብለዋል፡፡

ረዳት ፕሮፌሰሩ አክለውም በሀዋሳ ከተማ  ስር በሚገኙ በሁሉም መለስተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ሴት ተማሪዎች ተመሳሳይ ስልጠና ማግኘት እንዳለባቸው በመግልጽ፤ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስልጠና የወሰዱትን ተማሪዎች በቆይታቸው ያገኙትን እውቀት ለጓደኞቻቸው እንዲያካፍሉና ለትምህርታቸው ብቻ ትኩረት በመስጠት ከዚህ በኋላ የሚኖረው ሕይወታቸው የተማሩትን መምሰል ይገባዋል ብለዋል፡፡ ሴት ተማሪዎች በትምህርት ቤት ቆይታቸው ለሚገጥማቸው ማናቸውም ችግር ዳይሬክቶሬቱ ከጎን ሆኖ ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱንም ገልፀዋል፡፡

በዕለቱ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መለስተኛ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት አዳራሽ በተካሄደው በዚሁ ስልጠና ላይ ከትምህርት ቤቱ የተወጣጡ ከ40 በላይ ሴት ተማሪዎች መሳተፋቸው ታውቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et