የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒዩቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም በአኳ ካልቸር እና በዓሳ ሀብት ዙሪያ ከደቡብና ሲዳማ ክልል ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ በቦታው የተገኙት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

ፕሬዚዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ ሀገራችን የውሃ ማማ ተብላ የምትጠራ ቢሆንም እስከ አሁን ግን የውሃ ሀብቱን በሚፈለገው ልክ መጠቀም አለመቻሉን ገልጸው ይህንንም ሀብት ለመጠቀም መነሻ ሃሳቦችንና ምርምሮችን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመጀመር አኳ ካልቸር እና የዓሳ ሀብትንም ለማበልጸግ በትምህርት መደገፍ ስላለበት በዚህ ዙሪያ ከመጀመሪያ እስከ ሶስተኛ ድግሪ በማስተማር ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ትናንሽ ኩሬዎችን በማዘጋጀትና ዓሳን በማምረት ዓሳ ለገቢ ምንጭ፣ ለምግብ እና ለስራ ፈጠራ ማዋል እንደሚቻል ለህብረተሰቡና ለአርሶ አደሩ ሰርቶ ማሳያ አኳ ካልቸር ማዕከል መዘጋጀቱን እና  ወደፊትም ዩኒቨርሲቲው በዘርፉ የልህቀት ማዕከል እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

ተመራማሪና የአኳ ካልቸር ማዕከል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ካሳዬ ባልከው  እንደገለጹት እስካሁን በዘርፉ አኳ ካልቸር አዲስ በመሆኑ ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱን፣ ለአርሶ አደሩም እንደግብዓት የሚፈልጋቸውን የዓሳ ዝርያዎች በማከፋፈል ውጤቱ ምን እነደሚመስል ግብረመልስ በመውሰድ ውጤታማ መሆኑን እና የአኳ ካልቸር ግብዓቶችን በመስጠትና በማማከር  ዙሪያ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡

በምክከር መድረኩ ተሳታፊ የሆኑት የሀዋሳ ሃይቅ የዓሳ አስጋሪዎች ማኅበር ኃላፊ አቶ ዳዊት አብርሃምም በበኩላቸው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሀዋሳ ሃይቅ በጎርፍና በደለል መሞላቱን፣ በዙሪያው ላይ የእርሻ መስፋፋት እንዳለ እና ከኢንደስትሪ የሚለቀቁ ፈሳሾች ሃይቁን እየጎዱት መሆኑን በጥናት በማስቀመጥ ሃይቁንና በውስጡ ያሉትን ብዝሃ ሀብቶች ለመታደግ በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸው የዛሬውም የምክክር መድረክ የማህበሩ አባላት የተለያዩ ኩሬዎችን በማዘጋጀት ዓሳን ማምረት እንደሚቻልና ለሃይቃችንም የእፎይታ ጊዜ መስጠት እንደሚቻል ግንዛቤ ያገቸሁበት ነው ብለዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et