በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በምርምርና /ቴ/ሽ/ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ስር አራት ትላልቅ የስራ ዘርፎች ማለትም የምርምር ፕሮግራሞች፣ የቴ/ሽ/ዩ/ኢ/ ትስስር፣ የማህበረሰብ አገልግሎትና፤ የትብብር ፕሮጀክቶች ማስተባበሪያ ያሉ ሲሆን እነዚህም ስራዎች

በሁለት ኢንስቲትዩት፣በስምንት ኮሌጆችና ከአራት የተለያዩ ስራ ክፍሎች ጋር በትብብር የሚሰሩ ሲሆን በ2013 በጀት ዓመት ባለፉት 6 ወራት የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገም የምርምርና /ቴ/ሽ/ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት  በታህሳስ17/2013ዓ.ም የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡

በዕለቱም ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ የምርምርና /ቴ/ሽ/ም/ፕሬዚዳንት በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት ስራዎቻችን ለማከናወን መንግስት ከሚመድበው በጀት በተጨማሪ 60 ከሚሆኑ የትብብር ፕሮጀክቶች የሚገኝ በርካታ ሀብት የሚፈስ ሲሆን በም/ቴ/ሽ/ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት እና በተለያዩ ኮሌጆች፣ ኢንስቲትዩቶችና በማዕከላት መካከል ያለው ቅንጅትና መናበብ ወደሚፈለገው ደረጃ የደረሰ ባለመሆኑ በተለያዩ ስራ ክፍሎች መካከል ያለውን የመቀናጀትና የመናበብ ችግር ለመፍታት አብሮ ማቀድ እና  አፈጻጸሞችንም  በጋራ መገምገም አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ሆኖ  በመመረጡ በምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ቀጣይነት ያላቸው በርካታ ስራዎችን ለመስራት እስከአሁን ያለውን አፈጻጸማችንን እየገመገምን ለተሻለ ውጤት መትጋት ያለብን ሲሆን የዘርፉን አሰራር ለማሻሻል የተጀመሩ የተለያዩ ስራዎች በቀሩት ስድስት ወራትም ተጠናክረው የሚቀጥሉ እንደሚሆኑና መንግስት ባወጣው መመሪያ መሰረት በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ካለው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ካውንስል በተጨማሪ በኮሌጆችና ኢንስትቲዩቶች  ደረጃ የምርምርና ተክኖሎጂ ሽግግር ካውንስል የሚቋቋም መሆኑንም ምክትል ፕሬዚዳንቱ ተናጋረዋል፡፡

በመጨረሻም ሪፖረቶቹ ከቀረቡ በኃላ ባጋጠሙ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው ላይ ተሳታፊዎች በሰፊው ተወያይተው ፕሮግራሙ መጠናቀቁ ታውቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et