በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስኪል ላቦራቶሪ ማናጀር የሆኑት ኤፍሬም ጌጃ (ረ/ፕሮፌሰር) እንደገለጹት በተግባር ልምምድ ክፍላችን በዛሬው ዕለት እየተመዘኑ ያሉት ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው ሁሉ ልምምድ ሲያደርጉ
የቆዩ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን የጤና ተማሪዎች ሁሌም እንደሚያደርጉት ወደ ታካሚ ከመሄዳቸው በፊት በመማሪያ ክፍል ውስጥ የሸመቱትን እውቀት በተግባር ይለማመዳሉ፡፡ በመሆኑም ላለፉት አራት አመታት በዚህ ክፍል ሲለማመዱ የቆዩ የሰመመን ሰጪ ተመራቂ ተማሪዎች በአለም አቀፍ ደረጃ ወረርሺኝ በሆነው ኮቪድ 19 ምክንያት በ2012 ዓ.ም ልናስመርቃቸው የነበሩ ተማሪዎች ሲሆኑ በዛሬው ዕለት የግቢውን ማለፊያ ምዘና ለማከናወን ችለናል፡፡ በዚህም ምዘና ላይ የበኩላቸውን ሚና ለተወጡት የኮሌጁ ኃላፊዎች እና መምህራን ምስጋና ማቅረብ እንወዳለን፡፡ ኃላፊዎቹና መምህራኑ ለተመራቂ ተማሪዎች ሁልጊዜ ራሳቸውን በእውቀትና ክህሎት እያዳበሩ እንዲሄዱ ማሳሰቢያ በመስጠትና መልዕክት በማስተላለፍ ለሚሀሄዱበትም ሁሉ መልካም ዕድል ተመኝተውላቸዋል፡፡