የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት በማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት አማካኝነት በተመረጡ ወረዳዎች የተለያዩ የእንስሳትና የሰብል ቴክኖሎጂዎችን ለተጠቃሚዎች የማስተዋወቅና ተጠቃሚ  የማድረግ

ስራዎች እየሰራ ሲሆን በታህሳስ3/2013ዓ.ም በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ጨፌ ኮቲጃዌሳ ቀበሌ  ከኤስ ኦ ኤስ  የህጻናት መንደር ፕሮግራም ሀዋሳ  እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን የፍየል እርባታዎችን ለመጎብኘት የአርሶ አደሮች የመስክ በዓል አዘጋጅቷል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ከኤስ ኦ ኤስ  የህጻናት መንደር ፕሮግራም ሀዋሳ ጋር በጋራ በመሆን በዚህ ቀበሌ ከህብረተሰብ ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማድረግና ችግሮችን በመለየት በቂ ገንዘብ ለሌላቸው ወላጆች ዘላቂ ገቢ አግኝተው ኑሯቸው እንዲሻሻል߹ልጆቻቸውን በአግባቡ እንዲንከባከቡና እንዲያስተምሩ ገቢያቸውን መጨመር አስፈላጊ በመሆኑ የተለያዩ የክህሎትና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን  ከሰጠን በኃላ የተመረጡ የፍየል ዝርያዎችን እንዲያረቡ የሰጠን ሲሆን በዛሬው ዕለትም አርሶ አደሮቹ የተሰጣቸውን ዕድል በመጠቀም ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል አሳይተውናል ብለዋል፡፡

አቶ ጸጋዬ ደጀኔ የኤስ ኦ ኤስ  የህጻናት መንደር ፕሮግራም ዳይሬክተር ፕሮጀክቱ በዚሁ ቀበሌ አቅማቸው ለትምህርት ደርሶ የገንዘብ አቅም በማጣት ወደ ትምህርት ገበታ ያልገቡ 373 ተማሪዎችን እና 137 ተንከባካቢዎችን በመለየት የተለያዩ የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን በማበርከት ትምህርታቸውን እንዲጀምሩና እንዲከታተሉ  ከዩኒቨርሲቲው ጋር  በመሆን በርካታ ስራዎችን ሰርተናል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በስነ ምግባር የታነጹ እንዲሆኑ በሀይማኖት መሪዎች አማካይነት መንፈሳዊ እገዛ እንደተደረገላቸውም የቀበሌው ሊቀመንበር አቶ ዘለቀ ገልጸዋል፡፡

በመስክ ምልከታው ወቅት አርሶ አደሮቹ የተሰጧቸውን  ፍየሎች በማርባትና ወደገንዘብ በመቀየር ገቢ ማግኘታቸውን እና ኑሯቸው መሻሻሉን ገልጸው ለተደረገላቸው እርዳታም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et