ߵߵየትውልድ የስነ ምግባር ግንባታን በጠንካራ ዲሲፕሊን በመምራት ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን በሁሉም ዘርፍ በመታገል የብልጽግና ጉዟችንን እናፋጥናለንߴߴ በሚል መሪ ቃል የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በስነ ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት
በታህሳስ 2/2013ዓ.ም በዋናው ግቢ አከበረ፡፡
አቶ ከበደ ኩማ የስነ ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የዛሬው ዕለት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ17ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ እየተከበረ መሆኑን ገልጸው ሙስና በኢኮኖሚያዊ ߹ ፖለቲካዊ ና ማህበራዊ ዘርፎች እያስከተለ ያለውን ጉዳቶች ያብራሩ ሲሆን ከዚሁ ጎን ለጎን ስለ ሀብት ምዝገባ ምንነትና አስፈላጊነት በሰፊው የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የሀብት ምዝገባ ቅጽ አሞላል ላይ ለተሳታፊዎች ገለጻ ተደርጓል ፡፡