አካል ጉዳተኞችን አካታች߹ ምቹ߹ ዘላቂና የተሻለ ድህረ ኮቪድ-19 ዓለምን መልሶ መገንባት በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ለ29ኛ ጊዜ߹ በሃገራችን ለ28ኛ ጊዜና በዩኒቨርሲቲው ደግሞ ለ10ኛ ጊዜ በህዳር 26/2013ዓ.ም በዋናው ግቢ ተከብሯል፡፡

አቶ ተመስገን ከበደ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመክፈቻ ንግግራቸው በመሪ ቃሉ መሰረት የአካል ጉዳተኞችን እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ በዩኒቨርሲቲያችን በየደረጃው የሚታቀዱ ዕቅዶችና የሚሰጡ አገልግሎቶች

አካታችና እኩል ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ መሆን ይኖርባቸዋል ያሉ ሲሆን ዩኒቨርሲቲውም እስካሁን ለተቀበላቸው ተማሪዎች የተሟላ የምግብ߹ መኝታና የጤና አገልግሎቶችን በመስጠት እንዲሁም ለመማር ማስተማሩ ውጤታማነት የሚያገለግሉ የመማሪያ ግብዓቶችን በማሟላት የበኩላችንን ድርሻ እየተወጣንና በቀጣይም በአገልግሎት አሰጣጥና ተደራሽነት ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶችን በዕቅድ ለመፍታት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡  

በፕሮግራሙ ላይም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በአካል ጉዳተኞች ላይ ስለሚደርስባቸው ተግዳሮቶች ውይይት የቀረበ ሲሆን በዩኒበርሲቲው የሚወጡ ህጎች አካል ጉዳተኞች በተሳተፉበት ስለማይሆን ሲተገበሩ ክፍተቶች እንዳሉባቸው߹ የአካል ጉዳተኞች ማዕከል በዳይሬክቶሬት ደረጃ ማደግ እንዳለበት߹ የአካል ጉዳተኛ ሰራተኞችን እና የቅጥር ሁኔታ ላይ የጠቀመጡ መብቶች ተግባራዊ አለመሆናቸው እና ምን ያህል የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እንደሚገቡ እና ምን ያህሉ እንደሚባረሩ እንዲሁም ለምን ትምህርታቸውን እንደማያጠናቅቁ ሊጠና እንደሚገባ እና መሰል አስተያየትና ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች ተነስተው በሰፊው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በመጨረሻም በትምህርታቸው ላቅ ያለ ውጤት ላመጡ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸው ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡ 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et