ߵߵበሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን የማይታገስ ትውልድ እንፍጠርߴߴ በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ወይም የነጭ ሪቫን ቀን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በሴቶች߹ ህጻናት߹ ወጣቶችና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ጉዳዮች

ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በህዳር2/2013 ዓ.ም ተከብሯል፡፡

ይህን ቀን ስናከብር በአካባቢያችን߹ በሀገራችን እና በዓለማችን በሴቶች ላይ በየትኛውም ደረጃ የሚደርስባቸውን ማንኛውንም ጥቃት በመቃወምና ሴቶችም በማንኛውም የሥራ መስኮች ከወንዶች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የምንደግፍበትና ቃል የምንገባበት ቀንም ጭምር ነው በማለት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ አደቶ በመክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል፡፡

ወ/ሮ ምህረት ገነነ  የሴቶች߹ ህጻናት߹ ወጣቶችና ኤች.አይ.ቪ/አድስ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዓሉ በዓለማችን ለ29 በሀገራችን ደግሞ ለ15ጊዜ እየተከበረ መሆኑን ተናግረው ሴቶች በማህበረሰባችን ውስጥ በየትኛውም መስክ ያላቸው ድርሻ እጅግ ከፍተኛ ቢሆንም በተዛባ የስርዓተ-ጾታ አመለካከትና ጾታን መሠረት ባደረገና ሆን ተብሎ በሚፈጸሙ ጎጂ ድርጊቶች ምክንያት በርካታ ሴቶች ለአካላዊ߹ ማህበራዊ߹ ባህላዊ߹ ስነ-ልቦናዊ߹ ኢኮኖሚያዊ ለመሳሰሉት በርካታ ጉዳቶች ተጋላጭ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ አክልውም ሴቶች  በልማት߹ በመልካም አስተዳደር߹ በኢኮኖሚ߹ በፖለቲካው እና በመሳሰሉት ተሳትፏቸው እንዲጎለብት እየደረሰ ካለባቸው ጾታን መሠረት ካደረጉ ጉዳቶች ልንከላከላቸውና ልንደግፋቸው ይገባል ብለዋል፡፡  

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et