ዶ/ር በየነ ተክሉ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የካስኬፕ ፕሮጅክት አስተባባሪ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት አካባቢው ለተለያዩ አትክልትና ፊራፍሬ ልማት አመቺ ቢሆንም ከግንዛቤ ማነስ የተነሳ አርሶ አደሮቹ ሳያለሙ በመቆየታቸው ተጎጅ እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡
በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው ተገቢውን ጥናት ካደረገ በኋላ ከጌድኦ ዞን ግብርና ልማት መምሪ ጋር በመተባበር ካለፈው ዓመት ጀምሮ እንቅስቃሴ ውስጥ መገባቱን አስረድተው በአሁኑ ወቅት ከአርሶ አደሮች ከእህል ምርት በተጨማሪ አትክልትና ፍራፍሬ በማልማት ተጠቃሚ ለመሆን መብቃታቸውን አስረድተዋል፡፡ እንደ ዶ/ር በየነ ገለጻ የአርሶ አደሮቹን ምርት የተሻለ ገበያ እንዲያገኝ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የገበያ ትስስር በመፍጠር ላይ የሚገኙ ሲሆን በተለይም የአርሶ አደሮች ኀብረት ሥራ ማሕበራት ቀጥተኛ ተሳታፊ መሆናቸውን አስታውቀው በሌሎች አከባቢዎች የመኖሩ አርሶ አደሮችም የልምዲ ልውውጥ አድርገው ወደ ተግባር እንድገቡ የማስክጎብኘት ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ፕሮጀክቱ የሴቶችን ተጠቃሚነት ዋነኛ ዓላማ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ሲሆን በዚህም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የገጠር ሴቶች የገቢ ምንጭ በመፍጠር ተጠቃሚ ለማድረግ መቻሉን አስደረድተዋል፡፡ በልምድ ልውውጡ ሴት አርሶ አደሮች የተሳተፉ ሲሆን ከተሳትፊዎቹ መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት ፕሮጅክቱ በአከባቢያቸው በመጀመሩ በየጓሮቸው የተለዩ አዳዲስ ዝሪያ የአትክልትና ፍራፍሬዎችን በማልማት ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት በመቻላቸው መደሰታቸውን ገልፀው በቀጣይም በተሻለ መልኩ ለመሥራት መዘጋጀታቸውን አስረድተዋል፡፡