"ለመከላከያ_ክብር_እቆማለሁ” በሚል መርህ የኢትዮጵያ አርትስቶች ያዘጋጁት የመከላከያ ድጋፍ ዝግጅት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ከረፋዱ 5፡30 ላይ በተማሪዎች፣ በአስተዳደር ሠራተኞች እና በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር አካላት በደማቅ
ሁኔታ ተሳትፎ ተደርጓል፡፡ በግቢው ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የዝግጅቱ ሥነሥርዓት የተፈጸመ ሲሆን በዋናነት በዩኒቨርሲቲው የፕሬዝዳንት ሕንጻ ፊት ለፊት ከየቢሮአቸው በወጡ በርካታ ተሳታፊዎች እና በመማሪያ ክፍሎች አከባቢ በትምህርት ኮሌጅ መምህራንና ተመራቂ ተማሪዎች ጋር በድምቀት የድጋፍ ትዕይንት ተካሂዷል፡፡ በድጋፍ ትዕይንት ላይ የአትዮጵያ መዝሙር ተዘምሮ ከአርትስቶች በተዋረድ በተላለፈው መልዕክት መሠረት ለደቂቃዎች እጅ በልብ ላይ ተደርጎ ረዘም ያለ ጭብጨባም ለመከላከያ ክብር ተጨብጭቧል፡፡ በመጨረሻም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ ባራሶ እና የፕሮግራሙ መሪ የነበረው ተማሪ ብረሃነመስቀል ደሳለኝ “ አጨብጭበን ብቻ አንሄድም፤ ኢትዮጵያን ለዘላለም በልባችን እናኖራለን” በማለት ለድጋፍ ከየብሮአቸው ወጥተው ትዕይንቱን ያደመቁትን ተሳታፊዎች አመስግነው ሸኝተዋል፡፡