የ2012 ዓ.ም የሁለተኛ ሴሚስተር ት/ት ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ማጠቃለያ ውይይት ተካሄደ

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በCOVID-19 ቫይረስ ወረርሺን ምክንያት የተቋረጠውን የ2012 ዓ.ም የሁለተኛ ሴሚስተር ት/ት ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ማጠቃለያ ውይይት ተካሄደ፡፡ በዩኒቨርሲቲው ባሉ ሁሉም ኮሌጆች የተቋረጠውን ት/ት

ማስቀጠልን በተመለከተ ከመግበያ በሮች ጀምሮ በማደሪያ ክፍሎች፤በቤተመፃህፍት፤ቤተ ሙከራዎች እንዲሁም በካፍቴሪያዎች የተዘጋጀውን የCOVID19 መመሪያ በመከተል አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት የማድረግ ስራው በአብዛኛው የተጠናቀቀ ስለሆነ በቀሩት ጥቂት ቀናት የተቀሩትን የዝግጅት ስራዎች በማጠናቀቅ ተማሪዎችን በታቀደው መርሀግብር መቀበል እንደሚቻል ውሳኔ ላይ ተደርሷል፡፡

ተማሪዎች ምዝገባቸውን በ Online የሚያደርጉ ሲሆን ምንም አይነት የገጽ ለገጽ ምዝገባ አይኖርም፡፡ መታወቂያ እድሳትን በተመለከተ በት/ት ክፍሎች በሚወጣው መርሀግብር መሠረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡

ይህ ሁሉ ዝግጅት ቢደረግም ዋናው የጉዳዩ ባለቤት የሆኑት ተማሪዎቻችን መመሪያውን ካልተገበሩት ዝግጅቱ ፋይዳ የለውም፡፡ ስለዚህ ውድ ተማሪዎቻችን የሚናፍቋትን የምርቃት ቀን ለማየት እንዲሁም ሌሎችን ለመጠበቅ፤ መመሪያዎችን በጥብቅ ዲስፒልን እንዲፈፅሙ ከአደራ ጭምር እናሳስባን፡፡

ከምዝገባ ጋር ተያይዞ ያለውን ዝርዝር መረጃ በቅርብ ቀን የምናደርስ ይሆናል፡፡

#ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ #2013

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et