የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ስለኮሮና ቫይረስ በሽታ ምንነት፣ በበሽታው ላለመያዝ መወሰድ ስላለበት ቅድመ ጥንቃቄዎች እና በዓለም ላይ ብሎም በሀገራችን እያስከተለ ስላለው ጉዳቶች በሲዳማ ክልል በሚገኙ ዋና ዋና ከተማዎች

ማለትም ሀዋሳ፣ ይርጋለም፣ አለታወንዶ፣ ጩኮ፣ በንሳ ዳዬ፣ ሀገረሰላም፣ ቦና፣ ጠጥቻ፣ ለኩና ቦርቻ  በመዘዋወር ህብረተሰቡ በዘመን መለወጫና የመስቀል በዓላት ሳይዘናጋ ከኮሮና ወረርሽኝ እራሱን እንዲጠብቅ በመኪና ላይ የቅስቀሳና ለግንዛቤ መስጫ የሚረዳ በራሪ ወረቀቶችን በአማርኛና በሲዳምኛ ቋንቋዎች በማዘጋጀት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥቷል፡፡

ዶ/ር ዳኜ ሽብሩ የማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን  የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻውን አስመልክተው እንደ ሀገር የኮሮና ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝን ለመቀነስ እየተወሰደ ያለውን ዘመቻ በመደገፍ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም በወረርሽኙ ተጽዕኖ ምክንያት የኢኮኖሚ አቅማቸው ደካማ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚውል የምግብ ፍጆታና የንጽህና መጠበቂያ በማምረት ያበረከተ መሆኑን አስታውሰው ኮሌጁም የዩኒቨርሲቲው አንድ አካል በመሆኑ የድርሻውን ለመወጣት የተዘጋጀ ፕሮግራም መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አክለውም “የኮሮና ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝ በሀገር ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እኔም፣ አንተም፣ አንቺም፣ እርሶም ትልቅ አስተዋጽዖ ማድረግ እንችላለን“ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ መሆኑንና ይሄንን አስከፊ ወረርሽኝ ለመከላከል ብሎም በህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳቶችን ለመቀነስ የሁሉንም  ዜጎች ትብብርና ርብርብ እንደሚጠይቅ  ገልጸዋል፡፡

በፕሮግራሙም መወሰድ ስላለባቸው ቅድመ ጥንቃቄዎች ዜጎች አካላዊ ርቀታቸውን በመጠበቅ ባለመጨባበጥ፣ ባለመተቃቀፍና ንክኪን በመቀነስ ማህበራዊ ትስስራቸውን ማጠናከር እንደሚችሉ፤ በቤት ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ ጭንቀትን ለማስወገድ የመጽሐፍ ንባብ፣ አካላዊ እንቅስቃሴ፣ ሙዚቃ ማድመጥና ሌሎች ተግባራትን ማከናወንና መረጃዎችን ከትክክለኛ ምንጮች መስማት እንዳለባቸው፤ እንዲሁም መንግስት ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቀነስ የሚያስተላልፋቸውን መልዕክቶች መስማትና ተግባራዊ ማድረግ የሚሉት  ለግንዛቤ ማስጨበጫነት የተነሱ ነጥቦች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et