በጉዳዩ ላይ ለመምከር በዩኒቨርሲቲው የአፍሪካ ህብረት አደራሽ ነሐሴ 15 ቀን 2012 ዓ.ም በተካሄደ ዉይይት ላይ የፕሮጀክቱ አጥኝ ቡድን አስተባባሪ ዶ/ር ሙሉ ጌታ እንዳስታወቁት የማስተማሪያ ዘዴው ተማሪዎች ባሉበት ሆነው

በሞባይላቸው ላይ ባሉት መተገበሪያዎች በመጠቀም የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን በቀላሉ ለማግኘት የሚችሉ ከመሆናቸውም በላይ መምህራኖቻቸውን ጥያቄ መጠየቅም ሆነ መልስ ማግኘት እንደሚችሉ እንዲሁም እርስ በርሳቸው ጓደኝነት በመፍጠር መወያየት እንዲችሉ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡

በአዲሱ የማስተማሪያ ዘዴ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ክፍል በመመላለስ የሚያጠፉትን ጊዜ እንዲሁም ለህትመትና የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች ግዥ የሚዉለውን ከፍተኛ የገንዘብ ወጭ የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ በትምህርት ሂደቱ ላይ የሚፈጠሩ መሰላቸቶችን በመቅረፍ ተማሪው ደስተኛ ሆኖ እንዲማር የሚረዳ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የICT ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቴር አቶ እሱባለው ገ/ማርያም በበኩላቸው የማስተማርያ ዘዴውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ መሠረታዊ የመረጃ ቋቶችን የመሰብሰብ፤ የመተንተንና የማደራጀት ሥራዎች መጠናቀቃቸውንና ተማሪዎች በትምህርቱ ማጠናቀቂያ ላይ እንደየፍለጎታቸው ቴስቶችንም ሆኑ ማጠቃለያ ፈተና ወስደው ውጤታቸውን ወዲያው የሚያውቁበት ሁኔታዎችን የማመቻቸት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቴር ዶ/ር ባዩ ባንኩራ አሊቶ በበኩላቸው ለሀገራችን በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን ይህ የማስተማርያ ዘዴ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመስተዋወቅና የተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ጋር ተጣምረው ለሠራተኞቻቸው የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች የሚሰጡበት ሁኔታ ለማመቻት ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ በዚሁ ወቅት ባደረጉት የማጠቃለያ ንግግር በትምህርት ሂደቱ ላይ የነበሩ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ የመማር ማስተማሩን ሂደት የተሳለጠና ለተማሪዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም አማራጭ የሌለው መሆኑን ጠቁመው በቀጣይነት በጉዳዩ ዙሪያ መምህራን፤ ተማሪዎችና ሌሎችንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ዉይይት በማካሄድ አዲሱ የመማር ማስተማር ሥነ ዘዴ ተግባራዊ  እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡

በመጨረሻም ዩኒቨርሲቲው ዓለም የደረሰበትን የቴክኖሎጅ ፈጠራ ተግባራዊ ለማድረግና ለሀገር ልማት ለማዋል መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ከፕሬዝዳንቱ ገለፃ ለመረዳት ተችሏል፡፡  

    

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et