የ2012 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸምና የ2013 ዓ.ም መሪ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2013 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ላይ ውይይትና ግምገማ በነሐሴ 05/2012 ዓ.ም በዋናው ግቢ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ አካሄደ፡፡

ዶ/ር አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በመክፈቻ ንግግራቸው  እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ በዚህ ዓመትም ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማር፣ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎችን ለመሥራት አቅደን የተንቀሳቀስን ሲሆን በሃገሪቱ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከሚፈጠሩ አለመግባባቶች ጋር ተያይዞ በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥም የሰላምና ጸጥታ ችግሮች በመኖራቸው የመማር ማስተማሩ ሂደት የመቆራረጥና መስተጓጎል የታየበት መሆኑን ገልጸው በዩኒቨርሲቲያችን ግን በተቻለ መጠን ይህ ችግር እንዳይፈጠር በመሥራታችን የመጀመሪያው ሴሚስተርን በሰላም አጠናቀናል ብለዋል፡፡

ዶ/ር አያኖ ቀጥለውም በዓለም ላይ ሁላችንም እንደምናውቀው በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በሁለተኛ ሴሚስተር የጀመርነውን ትምህርት እንድናቋርጥ በመገደዳችን የመጀመሪያ ድግሪ ተማሪዎቻችንን ወደየመጡበት ምንም ችግር ሳይደርስባቸው የሸኘን ቢሆንም የሁለተኛ ድግሪ ተመራቂ ተማሪዎቻችንን ግን ጥንቃቄና ኃላፊነት  በተሞላበት መንገድ ትምህርታቸውን እንዲጨርሱ መደረጉን እና ሌሎች መደበኛ ሥራዎችም በአግባቡ የተሠሩ መሆናቸውንም ገልጸው በዕለቱም በሚቀርቡት  የአፈጻጸም ሪፖርትና የ2013 በጀት ዓመት  መሪ ዕቅድ ላይ ውይይትና ግምገማ በማድረግ ለቀጣይ በርትተን መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

በዕለቱም በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ጽ/ቤት በኩል የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይትና ግምገማ ከተካሄደ በኃላ የ2013 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ቀርቦም ውይይት የተካሄደ ሲሆን በአዲስ መልክ የቀረበው ዕቅድ እስከ ግለሰብ ወርዶ መታቀድ እንዳለበት ትኩረት ተሰጥቶ መጠናቀቁ ታውቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et