የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እና የደም ልገሳ ፕሮግራም ተካሄደ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እና የደም ልገሳ ፕሮግራም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በሰኔ 8/2012ዓ.ም አካሄደ፡፡

ዶ/ር አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በዕለቱ ተገኝተው እንደሀገር በዚህ ዓመት  አምስት ቢሊየን ችግኞችን  ለመትከል ዕቅድ የተያዘ ሲሆን ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድም በቅርቡ በሀዋሳ ከተማ በመገኘት በታቦር  ተራራ ላይ የችግኝ ተከላ  መረሃ ግብሩን ማሰጀመራቸውን አስታውሰው በዛሬው ዕለትም በዩኒቨርሲቲ ው ዋናው ግቢ አራት ሺህ አገር በቀል ችግኞን የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ በማስተባበር ለመትከል ተችሏል ብለዋል፡፡

ዶ/ር አያኖ አክለውም በቀጣይም በወንዶ ገነት በተፈጥሮ ሀብትና ደን ኮሌጅ ህብረተሰቡን በማስተባበርና ስራ አጥ ለሆኑ ወጣቶች የስራ ዕድል በመጠርም ወደፊት ለምግብነት የሚሆኑ አትክልቶችን ለመትከል እንዲሁም በቦርቻ የአካባቢ ጥበቃን በተመለከተ እና የአፈር መሸርሸርን ለማሰቀረት የሚያስችሉ ችግኞችን ለመትከል እቅድ የተያዘ መሆኑን ገልጸው ለረጅም ዓመታት ችግኞችን ለመትከል ብንሯሯጥም በተከልነው መጠን ግን ሲጸድቁ አይታይምና እንደሀገርም ሆነ እንደግለሰብ ችግኞችን እንደወለድናቸው ልጆች በመንከባከብ ልናሳድጋቸው እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ  በስተመጨረሻም በዓለም አቀፍ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ባስከተለው ቀውስ ለደም ባንክ የደምላጋሾች ቁጥር በመመናመኑ በየሆስፒታሎቹ  የደም እጥረት መከሰቱን ገልጸው እኛም እንደዜጋ ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነውና ከችግኝ ተከላው በተጓዳኝ ደም የለገስን ሲሆን ሌላውም የህብረተሰብ ክፍል ይህን መሱሉን ድጋፍ እንዲያደርግ እንጠይቃለን ብለዋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et