ዩኒቨርሲቲው ለኮሮና ቫይረስ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ቅድመ መከላከል ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የእጅ ንጽህና  መጠበቂያ ሳኒታይዘር ለዩኒቨርሲቲውና ለአከባቢው ማህበረሰብ እያቀረበ ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት ባሁኒ ዙር ወደ 20 ሺህ

የሚሆን ሳኒታይዘር በ100 ሚ.ሊ እና በ500 ሚ.ሊ በተለያየ መጠን በማምረት በሀዋሳ ከተማ ውስጥ በአስገዳጅ ሁኔታ ከቤታቸው ወጥተው ለመንግሥት ሥራ ለሚሰማሩና ቢሮ ለሚገቡ፣ እንዲሁም ለአካዳሚክ ስታፍ የማከፋፈሉን ሥራ በ07/09/12 ዓ.ም ጀምሯል፡፡

እንደሚታወቀው በ”WHO” ስታንዳርድ መሠረት በከፍተኛ ደረጃ ጥራቱን የጠበቀ በመሆኑ በአስተማማኝነት ዓላማውን የሚያሳካ ምርት መሆኑን በእደላው ወቅት የኬሚስትሪው ት/ክፍል ሀላፊ ዶ/ር አለማየሁ ለተጋበዙት የተለያዩ መሥሪያ ቤት ተወካዮችና ጋዜጠኞች አብራርተዋል፡፡ ዶ/ር ዘይቱ የተፈጥሮና ኮምፒተሽናል ሳይንስ ዲን በበኩላቸው በቀጣይነትም አስፈላጊው ግብዓት ተሟልቶ ጥራቱን የጠበቀ ሳኒታይዘር በማምረት ለተቀረውም ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብም ሆነ ለአከባቢው ህብረተሰብ በሰፊው ለማድረስ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et