የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2012ዓ.ም ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምሪፖርት ውይይት አደረገ

 የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ በዋናው ግቢ ከጥር 29/2012 ጀምሮ ለሁለት ቀናት ግምገማና ውይይት  አደረገ፡፡

ዶ/ር አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በመክፈቻ ንግግራቸው ዩኒቨርሲቲው እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ በዚህ ዓመትም ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማር፣ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን ገልጸው በሃገሪቱ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከሚፈጠሩ አለመግባባቶች ጋር ተያይዞ በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥም የሰላምና ጸጥታ ችግሮች በመኖራቸው የመማር ማስተማሩ ሂደት እየተቆራረጠና እየተስተጓጎለ ሲሆን በዩኒቨርሲቲያችን ግን በተቻለ መጠን ይህ ችግር እንዳይፈጠር በመሥራታችን የመጀመሪያው ሴሚስተርን በሰላም ያጠናቀቅን በመሆኑ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ሊመሰገን ይገባዋል ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አክለውም በዛሬው የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ግምገማና ውይይት በማድረግና ድክመቶቻችንን በማረም በቀጣይ ሁላችንም የተጣለብንን ኃላፊነት በመወጣት የተሻለ ሥራ መሥራት ይኖርብናል በማለት አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ውይይት ተደርጎ  አስተያየት የተሰጠባቸው ሲሆን ጠንካራና ደካማ ጎኖችንም በመለየት ቀጣይ አቅጣጫዎችንም በማሰቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

                                                                                                                                                                                                         በስለሺ ነጋሽ

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et