በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ "STEM" ማዕከል ከሲዳማ ብሔራዊ ክልል ሁሉም አካባቢዎች ለተውጣጡ 200 የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ላለፉት 15 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ልዩ ስልጠና ማጠቃለያ መርሃግብር ዛሬ ጠዋት በማዕከሉ ተካሂዷል::

መርሃግብሩን የከፈቱት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምር/ት/ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ ሲሆኑ ለሰልጣኞች ባስተላለፉት መልዕክት ወጣቱ ትውልድ ዘመኑን የዋጀ ለመሆን በሳይንስ: ቴክኖሎጂና ፈጠራ ላይ አስፈላጊውን እውቀትና ክህሎት መታጠቅ እንዳለበት አስገንዝበዋል:: ያለንበት ግዜ የሚፈልገውን እውቀት ያዳበረ ትውልድ ከተፈጠረ ሀገር ለመልማትና ከድህነት ለመውጣት የምታቅዳቸው ሥራዎችን ማቅለልና በዓለምአቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ ምሁራንን ማፍራት ወሳኝ እንደመሆኑ ዩኒቨርሲቲውም ከመደበኛው የመማር ማስተማርና የምርምር ሥራዎች እኩል የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሰል የአቅም ማጎልበቻ አገልግሎቶችን በየዓመቱ ለተለያዩ ተማሪዎች እየሰጠ መቆየቱን ም/ፕሬዝዳንቱ አስታውሰዋል::

የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂና እንግሊዝኛ ቋንቋን ጨምሮ በስድስት የትምህርት መስኮች ማለትም በሣይንስ: ቴክኖሎጂ ፈጠራና የሂሳብ ትምህርቶች ላይ በዩኒቨርሲቲው መምህራን ሲሰጥ የቆየው ስልጠና አላማ በዘርፉ ለሀገር እድገት አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ ወጣት የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን ማነቃቃትና ማዘጋጀት እንደሆነ የማዕከሉ አስተባባሪ ዶ/ር ዮናስ ሹኬ ተናግረዋል::

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et