በሶላር ኢነርጂ ላይ የሰለጠኑ ባለሙያዎች ተመረቁ

የወንዶገነት ደ/ተ/ሀ/ኮሌጅ በሶላር ኢነርጂ ላይ ያሰለጠናቸውን ባለሙያዎች አስመረቀ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደ/ተ/ሀ/ኮሌጅ በፀሐይ ብርሃን የሚሰራ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና ጥገና ላይ ያሰለጠናቸውን 21 ባለሙያዎች ዛሬ በሀዋሳ አስመርቋል::

የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ሳሙኤል በቀለ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት በኮሌጁ ካሉ የተለያዩ የትብብር ፕሮጀክቶች ዉስጥ በዚህ ታዳሽ ኃይል ላይ እየሰራ የሚገኘው የNORHED2 ReRed ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን ዓላማዉም ምርምር፣ ትምህርትና የአቅም ግንባታ ስልጠናን መስጠት መሆኑን ገልፀዋል:: በፕሮጀክቱ ድጋፍ በድህረ 3ኛ ድግሪ፣ በ3ኛ ድግሪ እና 2ኛ ድግሪ ትምህርታቸዉን እየተከታተሉ የሚገኙ መምህራን መኖራቸዉን፣ በኮሌጁ የሶላር ኃይል ማመንጫ ሰርቶ ማሳያ እና የዉሃ ኃይል ኤሌክትሪክ የሚያመነጭ አነስተኛ ግድብ እየተሰራ መሆኑን እንዲሁም ለተለያዩ ባለሙያዎች መሰል ስልጠናዎች መሰጠታቸዉን ዲኑ ተናግረዋል።

የዕለቱ የክብር እንግዳ የዩኒቨርሲቲዉ የትብብር ፕሮጀክቶች ማስተባበሪያ ዳይሬክተር ፕ/ር መብራቱ ሙላቱ በበኩላቸዉ ዩኒቨርሲቲዉ በመማር ማስተማር፣ በምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት እና ቴክኖሎጂዎችን በማመንጨትና በማስረፅ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ገልፀዉ በመንግስት በጀትና በትብብር ፕሮጀክቶች በሚገኙ ድጋፎች ማህበረሰቡን ለመደገፍ ከሚሰሩት ስራዎች ዉስጥ አንዱ የዚህ መሰሉ በየዘርፉ የሚገኙ ባለሙያዎችን በማሰልጠን የሰዉ ኃይል አቅም ማሳደግ መሆኑን ተናግረዋል:: ይህ በስልጠና የተገነባዉ አቅም ትርጉም ያለዉ ዉጤት የሚኖረዉ ማህበረሰቡ ዉስጥ ለዉጥ ሲያመጣ በመሆኑ ሰልጣኞችም ማህበረሰቡ ዉስጥ ለዉጥ የሚያመጣና የሚታይ ስራ እንዲያበረክቱ ፕ/ር መብራቱ አደራ ብለዋል።

የNORHED2 ReREd ፕሮጀክት ኃላፊው ዶ/ር ሽመልስ ንጋቱ እንደተናገሩት በፕሮጀክቱ አማካኝነት ከሲዳማ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ እና ከኦሮሚያ ክልሎች የተዉጣጡ 21የኢነርጂ ባለሙያዎች ይሄንን የአጭር ጊዜ ስልጠና በመዉሰድ ለዛሬዉ የምረቃ ቀን በቅተዋል። በተጨማሪም የሲዳማ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋ/ዳይሬክተር አቶ መስፍን ምጩቄ የሰዉ ኃይል ማብቃትና አቅም ማጎልበት ወሳኝ መሆኑን ዩኒቨርሲቲዉ ተረድቶ የዚህ መሰሉን ስልጠና እየሰጠ በመሆኑ ሊመሰገን ይገባዋል ብለዋል።

በመጨረሻም በታዳሽ ኃይል ዙሪያ የተሰሩ ሥራዎች ጉብኝት ተካሂዶ እና ሰልጠናዉን ላጠናቀቁ ባለሙያዎች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸው ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et