ለዲጅታል ቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ስራዎች የውል ስምምነት ተፈረመ

ለዲጅታል ቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ስራዎች የውል ስምምነት ተፈረመ::

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከሲዳማ ክልል ገቢዎች ቢሮ ጋር የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን ለማዘመን የሚያስችል የዲጅታል ቴክኖሎጂ (የሶፍትዌር ማበልፀግ) ሥራ የውል ስምምነት ጥር 24 ቀን 2016 ዓም ተፈራርሟል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር አያኖ በራሶ በስምምነቱ ወቅት እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው ለክልሉ በርካታ የማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎችን እየሰራ እንዳለና በሀገር አቀፍ ደረጃም ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ተረክቦ በጥራት በማጠናቀቅ የሚታወቅ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን የመማሪያ መፃህፍት ዝግጅት እንደምሳሌ ጠቅሰዋል:: ፕሬዚደንቱ እንዳሉት ለባለሙያዎች ከሚያስፈልገው የሙያ ክፍያ ባሻገር ዩኒቨርሲቲው ምንም ትርፍ ሳይፈልግ ክልሉን እንደሚያገለግልና ስራውን በከፍተኛ ጥራት በአጭር ግዜ አጠናቆ እንደሚያስረክብ ቃል ገብተዋል:: በንግግራቸው ማጠቃለያም ሶፍትዌር ማበልፀግ አንድ ግዜ ተሰርቶ የሚያልቅ ሳይሆን ተከታታይ ድጋፍና ማሻሻያ የሚፈልግ እንደመሆኑ እኛ ሰርተን ከማስረከብ ባለፈ ያልተቋረጠ ቀጣይ ሙያዊ እንደምናደርግላችሁ እርግጠኛ መሆን ትችላላችሁ ካሉ በኃላ ግን ከናንተ በኩል ቴክኖሎጂውን ለመተግበር የሚያስችል በቂ መሰረተልማት ማሟላት እንዲሁም የእውቀት ሽግግር እንዲኖር ባለሙያዎችን መመደብ ይጠበቃል ብለዋል::

የሲዳማ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ ጉዱራ በበኩላቸው ክልሉ  ከተመሠረተ በአጭር  ጊዜ ውስጥ የወጪዎቹን ግማሽ (50%) በውስጥ ገቢው ለመሸፈን የሚያስችል አቅም መፍጠር የቻለ ቢሆንም በስራ ሂደት ላይ ያጋጠሙ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ጉድለቶች ማስተካከል እንዳስፈለገ ገልፀዋል። ችግሩን ለማቃላል በወጣዉ ውስን ጨረታ ከተሳተፉት አምስት የሀገር ውስጥ የከፍተኛ ት/ተቋማት መካከል ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ልዩነት በማሸነፉ  ወደ ስራ ውል ስምምነት መገባቱን ኃላፊው ገልፀዋል። ዩኒቨርሲቲው የገቢ አቅምን ለማሳደግ የሚረዳ ምርምር ከመስራት አንስቶ በርካታ ድጋፎችን ለክልሉ እያበረከተ መሆኑን ጠቅሰው ከድጅታል ቴክኖሎጂው በተጨማሪ ሌሎች ስራዎችን አብረው እንደሚሰሩ ኃላፊው ተናግረዋል::

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et