የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፣ አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እና ኖርዌጂያን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ በጋራ ባላቸው የ Ethiopian Norwegian Network in Computational Mathematics (ENNCoMat)   ፕሮጀክት  በ2017 ዓ/ም በመደበኛዉ መርሀ ግብር ከዚህ በታች በተጠቀሱት ፕሮግራሞች በሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

  1. Master of Science in Mathematical Modelling

ፕሮግራሙ የሚሰጥበት ቦታ ፡-C

ብዛት ፡- 1

  1. Master of Science Degree in Applied Mathematics

ፕሮግራሙ የሚሰጥበት ቦታ ፡_ Adama Science and Technology University

ብዛት ፡- 1

  1. Master of Science in Computational Mathematics

ፕሮግራሙ የሚሰጥበት ቦታ ፡_ Hawassa University

ብዛት ፡- 1

 የማመልከቻ መስፈርቶች

  • አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ድግሪ ያለዉ/ያላት
  • በ 2016 ዓ.ም የGAT ፈተና ወስዶ/ዳ በትምህርት ሚኒስተር የተቀመጠውን የማለፊያ ነጥብ ያመጣ/ያመጣች
  • አግባብነት ካላቸዉ ተቋማት 3 የድጋፍ ደብዳቤዎች ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  • ዩኒቨርሲቲዉ የሚያወጣዉን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል
  • ቀደም ሲል ከተማሩበት የትምህርት ተቋም ኦፊሺያል ትራስክሪፕት ማስላክ የሚችል/የምትችል
  • አግባብነት ካላቸዉ ተቋማት የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  • የስፖንሰር ሽፕ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል የምትችል
  • ኖርዌይ በሚገኘው ተባባሪ የኒቨርስቲ ከስድስት ወር እስከ አስር ወር ድረስ የሚሰጠውን የትምህርት ስልጠና ለመውስድ ፍቃደኛ የሆነ/የሆነች እንዲሁም ለጉዞ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች ከመጋቢት 30/2016 ዓ.ም ድረስ ማቅረብ የሚችል/የምትችል

ማሳሰቢያ፡-

  • ምዝገባው የሚከናወነው በኦላይን ብቻ ሲሆን ምንም አይነት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ማስገባት አይቻልም፡፡
  • አመልካቾች ከታህሳስ 25-ጥር 17 /2016 ዓ.ም የማመልከቻ ፎርሙን በሚከተለው ቅጽ (https://forms.gle/m64cYX6qTK7dez8SA) ላይ በመግባት መረጃዎችን መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
  • አመልካቾች በ ፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን፣ የትምህርት ወጪዎን /Sponsorship/ የሚሸፍንልዎት የመንግስት መስሪያ ቤት የተፈረመበትና ማህተም የተደረገበት ፎርም እና ሌሎች መረጃዎችን በማያያዝ  ምዝገባዎትን ማጠናቀቅ ይኖርብዎታል፡፡
  • የመግቢያ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች ከተማሩበት ተቋም ኦፊሺያል ትራስክሪፕታቸዉ ወደ አመለከቱበት ዩንቨርሲቲዉ ሬጅስትራርና አሉምናይ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ማስላክ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በምዝገባ ወቅት ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ካልደረሰ መመዝገብ አይችሉም።
  • የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን በቀጣይ የሚገለጽ ይሆናል።
  • የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው ያለፉ ተማሪዎች ባለፉበት ዩኒቨርስቲ ማሟላት ያለባቸውን መረጃ አሟልተው አድሚሽን የሚሰጣቸው ሲሆን በመጨረሻም ትምህርታቸውን ሲጨርሱ አድሚሸን ከሰጣቸው ዩኒቨርስቲ የትምህርት ማስረጃቸው የሚሰጥ ይሆናል።
  • የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው ያለፉ ተማሪዎች ኖርዌይ ሄደው በሚማሩበት ጊዜ የሚኖሩበትንና የትራንስፖርት ወጪዎችን በውሉ መሰረት ፕሮጀክቱ የሚሸፍን ይሆናል።
  • የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው ያለፉ ተማሪዎች ሀገር ውስጥ በሚኖሩበት ወቅት ስፖንሰር የሌላቸው ከሆነ አነስተኛ የኪስ ገንዘብ ፣ የወጪ መጋራት ክፍያ ፣ የትምህርት ወጪዎችን እና የምርምር ወጪዎችን ፕሮጀክቱ የሚሸፍን ይሆናል።

ENNCoMat ፕሮጀክት አስተባባሪ

 To download the PDF click here

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et