በ2015 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ ሬመዲያል (Remedial Program) የተመደባችሁ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ የመግቢያ ጊዜ ከየካቲት 30-መጋቢት 01/ 2015 ዓ.ም መሆኑን ይገልጻል።
የምደባ ቦታ፡-
- በ Social Science የተመደባችሁ የስማችሁ መነሻ ፊደል ከ A-L በቴክኖሎጂ ኢንስቲቱዩት ግቢ እንዲሁም ከM-Z በዋናው ግቢ
- በ Natural Science የተመደባችሁ የስማችሁ መነሻ ፊደል ከ A-E በበንሳ ዳዬ ግቢ ፣ ከ F-P በግብርና ኮሌጅ ግቢ እንዲሁም ከ R-Z በዋናው ግቢ
የተመደባችሁ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሰው ቦታ በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰብያ ፡- ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ የሚከተሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
1ኛ. የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ቅጂው
2ኛ. ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክርቢት ዋናውና ቅጂው
3ኛ. የሌሊት አልባሳት
4ኛ. 4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ
5ኛ. የስፖርት ትጥቅ
ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር እና አልሙኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት