በ2014ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያም በላይ አምጥታችሁ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች  ምዝገባ  በበየነ መረብ ”Online”  ከየካቲት 20-26/2015 ዓ.ም ድረስ የሚከናወን ሲሆን  የተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ  የመግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ የካቲት 27-28/2015 ዓ.ም በዋናው ግቢ መሆኑን ይገልጻል፡፡

ማሳሰቢያ

  • ስለምዝገባ ሂደቱ ዝርዝር መረጃዎችን በዩኒቨርስቲዉ ድህረ-ገጽ https://hu.edu.et እና በዩኒቨርስቲው የማህበራዊ ገጾች የሚገለጹ መሆኑን ያሳዉቃል፡፡
  • ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ የሚከተሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡

1ኛ.  የ12ኛ  ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ቅጂው

2ኛ.  ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክርቢት ዋናውና ቅጂው

3ኛ.  የሌሊት አልባሳት

4ኛ.  4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ

5ኛ. የስፖርት ትጥቅ

  • በተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2015 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ የካቲት 29 እና 30 2015 ዓ.ም እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡
  • ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡

  የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ  ሬጅስትራር እና አልሙኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et