ማስታወቂያ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ/ም በ2ኛ ሴሚስተር በመደበኛዉ መርሀ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች በሁለተኛ ዲግሪ እና በሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ቀን 28/04/15 ዓ.ም

 የማመልከቻ መስፈርቶች

 • ለሁለተኛ ዲግሪ አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ድግሪ ያለዉ/ያላት
 • ለሶስተኛ ዲግሪ አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ ሁለተኛ ድግሪ ያለዉ/ያላት
 • አግባብነት ካላቸዉ ተቋማት 3 የድጋፍ ደብዳቤዎች ማቅረብ የሚችል/የምትችል
 • ዩኒቨርሲቲዉ የሚያወጣዉን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል
 • ቀደም ሲል ከተማሩበት የትምህርት ተቋም ኦፊሺያል ትራስክሪፕት ማስላክ የሚችል/የምትችል
 • አግባብነት ካላቸዉ ተቋማት የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል

 ማሳሰቢያ፡-

 • ምዝገባው የሚከናወነው በኦላይን ወይም በአካል በመቅረብ ማመልከት ይቻላል፡፡
 • የማመልከቻ ጊዜ ከጥር 01-19 /2015 ዓ.ም
 • አመልካቾች የንግድ ባንክ ቁጥር 1000013481788 በመጠቀም የማመልከቻ ክፍያ 250 ብር መክፈል ይጠበቅባቸል።
 • በኦላይን ለሚያመለክቱ የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲው የፖርታል ገጽ (https://portal.hu.edu.et) አካውንት በመፍጠር አስፈላጊዎችን መረጃዎችን በመሙላት ማመልከት ይችላለሁ።
 • በአካል ቀርበው ለሚያመለክቱ ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 41 በመቅረብ የማመልከቻ ቅጹን በመውሰድና በመሙላት አስፈላጊውን ማስረጃዎቻቸውን በማያያዝ ማመልከት ይችላሉ።
 • በኦላይን የሚያመለክቱ አመልካቾች ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመልከቻ ፎርሙ በመመለስ ፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን፣ ባንክ የከፈሉበትን ደረሰኝ እንዲሁም የትምህርት ወጪዎን /Sponsorship/ የሚሸፍንልዎት የመንግስት መስሪያ ቤት ከሆነ የተፈረመበትና ማህተም የተደረገበት ፎርም እና ሌሎች መረጃዎችን በማከልና በማማያዝ  ምዝገባዎትን ማጠናቀቅ ይኖርብዎታል፡፡ እንዲሁም በአካል ቀርበው የሚያመለክቱ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማያያዝ ይጠበቅባችዋል።
 • የመግቢያ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች ከተማሩበት ተቋም ኦፊሺያል ትራስክሪፕታቸዉን ወደ ዩንቨርሲቲዉ ሬጅስትራርና አሉምናይ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በኢሜል (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.) ማስላክ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በምዝገባ ወቅት ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ካልደረሰ መመዝገብ አይችሉም
 • የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ጥር 26/2015 ዓ.ም በየኢንስቲቲዩትና ኮሌጆች ይሆናል፡፡
 • በመንግስት ተቋማት እስፖነሰር የሚደረግ አመልካች የትምህርት ወጪው ዩኒቨርስቲው በሚጠይቀው የክፍያ መጠን መሰረት በየሴሚስተሩ በምዝገባ ወቅት ክፈያው መፈጸም ይኖርበታል።
 • የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

2015 . የትምህርት ዘመን 2 ሴሚስተር ቅበላ የሚከናወንባቸው የሁለተኛ እና ሶሰተኛ ዲግሪ የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች።

 1. College of Agriculture
 • MSc in Animal Nutrition
 • MSc in Rangeland Ecology and Management
 • MSc in Animal Breeding and Genetics
 • MSc in Plant Breeding
 • MSc in Plant Pathology
 • MSc in Soil Science
 • MSc in Crop Protection
 • MSc in Bio-energy Science and Technology
 • MSc in Plant Bio-technology
 • MSc in Agroforestry
 • MSc in Agricultural Management
 • MSc in Gender and Family Studies
 • MSc in Food Safety and Quality Management
 • PhD in Animal Nutrition
 • PhD in Horticulture
 • PhD in Food Science and Technology
 • PhD in Soil Science
 1. College of Natural and Computational Science
 • MSc in Aquaculture and Fisheries Management
 • PhD in Applied Statistics
 • PhD in Organic Chemistry
 • PhD in Aquatic Sciences, Fisheries & Aquaculture
 1. Institute of Technology
 • MSc in Irrigation & Drainage Engineering
 • MSc in Water Resources Engineering and Management
 • MSc in Hydrology and Water Resources Engineering
 • MSc in Water Supply and Environmental Engineering
 • MSc in MSc. in Education Technology and Innovation (New)
 • PhD in Agricultural Engineering
 1. College of Social Sciences and Humanities
 • MA in Educational Assessment and Evaluation
 1. College Law and Governance
 • MA in Governance & Development Studies
 • MA in Peace and Conflict Studies
 • MA in Public Management and Policy Development
 • M. in Land and Environmental Law
 • M. in Criminal Justice
 1. College of Education
 • MA in Educational Supervision and Quality Management
 • MA in Adult Education and Community Development
 1. Wondo Genet College of Forestry and Natural Resources
 • MSc in Watershed Management
 • MSc in Natural Resource Economics & Policy
 • MSc in Urban Forestry
 • PhD in Agroforestry
 • PhD in Wildlife Ecology (Specialization: Ornithology, Mammalogy)
 • MSc in Forest Resource Assessment and Monitoring
 • MSc in Wildlife Ecology and Conservation
 • MSc in Climate Smart Agriculture and Landscape Assessment

 ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራርና አሉሚኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et