ማስታወቂያ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች  ምዝገባ  በበየነ መረብ ”Online”  ከግንቦት 01-05/2014 ዓ.ም ድረስ የሚከናወን ሲሆን  የተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ  የመግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ግንቦት 08-09/2014 ዓ.ም በዋናው ግቢ መሆኑን ይገልጻል፡፡

ማሳሰቢያ፦

  1. ስለምዝገባ ሂደቱ ዝርዝር ማመልከቻውን ሂደት ቅደም ተከተል ለማውረድ ይህንን ይጫኑ
  2. ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ የሚከተሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡

             1ኛ.  የ12ኛ ና 10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ቅጂው

             2ኛ.  ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክርቢት ዋናውና ቅጂው

             3ኛ.  የሌሊት አልባሳት

             4ኛ.  አራት (4) ጉርድ ፎቶ ግራፍ

             5ኛ.  የስፖርት ትጥቅ

  1. በተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2014 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ግንቦት 10 እና 11 2014 ዓ.ም እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡
  2. ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡   

ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ ሪፖርት የማድረጊያ ጊዜ ግንቦት 08-09/2014 ዓ.ም ሲሆን
1. በ Natural Science and Teacher Education in Natural Science የተመደባችሁ በዋናው ግቢ
2. በ Social Sciences Teacher Education in Social Science የተመደባችሁ በቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት(IOT) መሆኑን እናሳውቃለን።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ  ሬጅስትራር እና አልሙኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et