ማስታወቂያ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፣ አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እና ኖርዌጂያን ሳይንስና ቴክኖሎጂ የኒቨርስቲ በጋራ ባላቸው የ Ethiopian Norwegian network in computational mathematics (ENNCoMat)   ፕሮጀክት  በ2015 ዓ/ም በመደበኛዉ መርሀ ግብር ከዚህ በታች በተጠቀሱት ፕሮግራሞች በሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

  1. Master of Science in Mathematical Modeling

               ፕሮግራሙ የሚሰጥበት ቦታ ፡-Arba Minch University

               ብዛት ፡- 1

  1. Master of Science Degree in Applied Mathematics

             ፕሮግራሙ የሚሰጥበት ቦታ ፡_ Adama Science and Technology University

             ብዛት ፡- 1

  1. Master of Science in Computational Mathematics

           ፕሮግራሙ የሚሰጥበት ቦታ ፡_ Hawassa University

           ብዛት ፡- 1

 የማመልከቻ መስፈርቶች

  • አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ድግሪ ያለዉ/ያላት
  • አግባብነት ካላቸዉ ተቋማት 3 የድጋፍ ደብዳቤዎች ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  • ዩኒቨርሲቲዉ የሚያወጣዉን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል
  • ቀደም ሲል ከተማሩበት የትምህርት ተቋም ኦፊሺያል ትራስክሪፕት ማስላክ የሚችል/የምትችል
  • አግባብነት ካላቸዉ ተቋማት የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  • የስፖንሰር ሽፕ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል የምትችል
  • ኖርዌይ በሚገኘው ተባባሪ የኒቨርስቲ ከስድስት ወር እስከ አስር ወር ድረስ የሚሰጠውን የትምህርት ስልጠና ለመውስድ ፍቃደኛ የሆነ/የሆነች እንዲሁም ለጉዞ የሚያስፈለረጉ ዶክመንቶች በሚጠየቅ ጊዜ ማቅረብ የሚችል/የምትችል

ማሳሰቢያ፡-

  • ምዝገባው የሚከናወነው በኦላይን ብቻ ሲሆን ምንም አይነት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ማስገባት አይቻልም፡፡
  • አመልካቾች ከመጋቢት 01-15 /2014 ዓ.ም የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲው ድረገጽ (https://portal.hu.edu.et) አካውንት በመፍጠር አስፈላጊዎችን መረጃዎችን መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
  • አመልካቾች በ ፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን፣ የትምህርት ወጪዎን /Sponsorship/ የሚሸፍንልዎት የመንግስት መስሪያ ቤት የተፈረመበትና ማህተም የተደረገበት ፎርም እና ሌሎች መረጃዎችን በማከልና በማማያዝ  ምዝገባዎትን ማጠናቀቅ ይኖርብዎታል፡፡
  • የመግቢያ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾ ከተማሩበት ተቋም ኦፊሺያል ትራስክሪፕታቸዉ ወደ አመለከቱበት ዩንቨርሲቲዉ ሬጅስትራርና አሉምናይ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ማስላክ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በምዝገባ ወቅት ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ካልደረሰ መመዝገብ አይችሉም።
  • የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን በማስታወቂያ የሚገለጽ ሲሆን ፈተናው በተመሳሳይ ቀንና ሰአት የሚሰጥ በመሆኑ ከአንድ ዩኒቨርስቲ በላይ ማመልከት አይቻልም፡፡
  • የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው ያለፉ ተማሪዎች ባለፉበት ዩኒቨርስቲ ማሟላት ያለባቸውን መረጃ አሟልተው አድሚሽን የሚሰጣቸው ሲሆን በመጨረሻም ትምህርታቸውን ሲጨርሱ አድሚሸን ከሰጣቸው ዩኒቨርስቲ የትምህርት ማስረጃቸው የሚሰጥ ይሆናል።
  • የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው ያለፉ ተማሪዎች ኖርዌይ ሄደው በሚማሩበት ጊዜ የትራንስፖርትን ጨምሮ የሚኖሩ ወጪዎችን በውሉ መሰረት ፕሮጀክቱ የሚሸፍን ይሆናል።
  • የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው ያለፉ ተማሪዎች ሀገር ውስጥ በሚኖሩበት ወቅት የሚኖሩ የትምህርት ወጪዎችን እና የምርምር ወጪዎችን ፕሮጀክቱ አይሸፍንም። 

ENNCoMat ፕሮጀክት አስተባባሪ

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et