ማስታወቂያ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ/ም ሁለተኛ ሴሚስተር ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች በሁለተኛ ዲግሪ እና በሶስተኛ ዲግሪ በመደበኛው ፕሮግራም ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

College of Agriculture

    MSc in Bio-energy Science and Technology

    MSc in Agroforestry

    MSc in Gender and Family Studies

    MSc in Food Safety and Quality Management

 College of Natural and Computational Science

    MSc in Genetics

    MSc in Veterinary Parasitology

    Ph.D. in Genetics and Genomics

    Ph.D. in Applied Microbiology

College of Medicine and Health Science

    MSc in Hospital and Health Care Administration

    MSc in Medical Biochemistry

Institute of Technology

    MSc in Soil and Water Conservation Engineering

    MSc in Hydrology and Water Resources Engineering

    MSc in Dam Engineering

    Ph.D. in Natural Resource Engineering & Management

 College Law and Governance

    MA in Governance and Development

    MA in Public Management and Policy Development

College of Education

    MA in Educational Research and Development

    MA in Multicultural and International Education

Wondo Genet College of Forestry and Natural Resources

    MSc in Climate Smart Agricultural Land Assessment

    MSc in Forest Resources Assessment and Monitoring

    MSc in Production Forestry

    MSc in Urban Forestry and Greening

    PhD. in Agroforestry

    Ph.D. in Forest Management 

    Ph.D. in Forest Ecology and Silviculture

    Ph.D. in Wildlife Ecology (Specialization: Ornithology, Mammalogy)

  የማመልከቻ መስፈርቶች

  • ለሁለተኛ ዲግሪ አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ድግሪ ያለዉ/ያላት
  • ለሶስተኛ ዲግሪ አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ ሁለተኛ ድግሪ ያለዉ/ያላት
  • አግባብነት ካላቸዉ ተቋማት 3 የድጋፍ ደብዳቤዎች ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  • ዩኒቨርሲቲዉ የሚያወጣዉን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል
  • ቀደም ሲል ከተማሩበት የትምህርት ተቋም ኦፊሺያል ትራስክሪፕት ማስላክ የሚችል/የምትችል
  • አግባብነት ካላቸዉ ተቋማት የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል

ማሳሰቢያ፡-

  • ምዝገባው የሚከናወነው በኦላይን ብቻ ሲሆን ምንም አይነት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ማስገባት አይቻልም፡፡
  • አመልካቾች ከጥር 09-20/2014 ዓ.ም የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲው ድረገጽ (https://portal.hu.edu.et) አካውንት በመፍጠር አስፈላጊዎችን መረጃዎችን መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
  • አመልካቾች የንግድ ባንክ ቁጥር 1000013481788 በመጠቀም የማመልከቻ ክፍያ 250 ብር መክፈል ይጠበቅባቸል።
  • ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመልከቻ ፎርሙ በመመለስ ፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን፣ ባንክ የከፈሉበትን ደረሰኝ እንዲሁም የትምህርት ወጪዎን የሚሸፍንልዎት የመንግስት መስሪያ ቤት ከሆነ የተፈረመበትና ማህተም የተደረገበት የSponsorship ፎርም እና ሌሎች መረጃዎችን በማከልና በማማያዝ ምዝገባዎትን ማጠናቀቅ ይኖርብዎታል፡፡
  • የመግቢያ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾ ከተማሩበት ተቋም ኦፊሺያል ትራስክሪፕታቸዉ ወደ ዩንቨርሲቲዉ ሬጅስትራርና አሉምናይ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ማስላክ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በምዝገባ ወቅት ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ካልደረሰ መመዝገብ አይችሉም
  • የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ጥር 30/ 2014 ዓ.ም በየኮሌጆቹ ይሆናል፡፡
  • በመደበኛ ፕሮግራም በመንግስት ተቋማት እስፖነሰር የሚደረግ አመልካች የትምህርት ወጪው ዩኒቨርስቲው በሚጠይቀው የክፍያ መጠን መሰረት በየሴሚስተሩ በምዝገባ ወቅት ክፈያው መፈጸም ይኖርበታል።
  • የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

 ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራርና አሉሚኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et