የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ/ም አዳዲስ በሚከፈቱ እና በነባር ፕሮግራሞችና በመደበኛዉ መርሀ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች በሁለተኛ ዲግሪ እና በሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
የማመልከቻ መስፈርቶች
- ለሁለተኛ ዲግሪ አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ድግሪ ያለዉ/ያላት
- ለሶስተኛ ዲግሪ አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ ሁለተኛ ድግሪ ያለዉ/ያላት
- አግባብነት ካላቸዉ ተቋማት 3 የድጋፍ ደብዳቤዎች ማቅረብ የሚችል/የምትችል
- ዩኒቨርሲቲዉ የሚያወጣዉን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል
- ቀደም ሲል ከተማሩበት የትምህርት ተቋም ኦፊሺያል ትራስክሪፕት ማስላክ የሚችል/የምትችል
- አግባብነት ካላቸዉ ተቋማት የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
ማሳሰቢያ፡-
- ምዝገባው የሚከናወነው በኦላይን ብቻ ሲሆን ምንም አይነት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ማስገባት አይቻልም፡፡
- አመልካቾች ከነሐሴ 24 /2013 - መስከረም 06/2014 ዓ.ም የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲው ድረገጽ (https://portal.hu.edu.et) አካውንት በመፍጠር አስፈላጊዎችን መረጃዎችን መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
- አመልካቾች የንግድ ባንክ ቁጥር 1000013481788 በመጠቀም የማመልከቻ ክፍያ ማለትም ለሁለተኛ ዲግሪ አመልካቾች 250 ብር ለሶስተኛ ዲግሪ አመልካቾች 1000 ብር መክፈል ይጠበቅባቸል።
- ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመልከቻ ፎርሙ በመመለስ ፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን፣ ባንክ የከፈሉበትን ደረሰኝ እንዲሁም ለቀን መርሃ ግብር የትምህርት ወጪዎን /Sponsorship/ የሚሸፍንልዎት የመንግስት መስሪያ ቤት ከሆነ የተፈረመበትና ማህተም የተደረገበት ፎርም እና ሌሎች መረጃዎችን በማከልና በማማያዝ ምዝገባዎትን ማጠናቀቅ ይኖርብዎታል፡፡
- የመግቢያ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾ ከተማሩበት ተቋም ኦፊሺያል ትራስክሪፕታቸዉ ወደ ዩንቨርሲቲዉ ሬጅስትራርና አሉምናይ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ማስላክ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በምዝገባ ወቅት ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ካልደረሰ መመዝገብ አይችሉም
- የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን መስከረም 14/ 2014 ዓ.ም በየኮሌጆቹ ይሆናል፡፡
- በመደበኛ ፕሮግራም በመንግስት ተቋማት እስፖነሰር የሚደረግ አመልካች የትምህርት ወጪው ዩኒቨርስቲው በሚጠይቀው የክፍያ መጠን መሰረት በየሴሚስተሩ በምዝገባ ወቅት ክፈያው መፈጸም ይኖርበታል።
- የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- መስኮቹን ዝርዝር ከዚህ በታች ይመልከቱ
በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ የሚከፈቱና የሚሰጡ የሁለተኛ እና ሶሰተኛ ዲግሪ የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች
College of Agriculture
- PhD in Agricultural Economics (Specialization: Agricultural Production and Environmental Economics, Agricultural Marketing and Trade Economics, Natural Resources and Energy Economics)
- PhD in Dairy Science and Technology
- PhD in Livestock Science and Production (Specialization: Dairy Science and Production, Meat Science and Production, Poultry Science and Production)
- MSc in Agricultural Management
College of Natural and Computational Science
- PhD in Quantum Optics
- Master of Veterinary Science in Clinical Medicine
- MSc in Inorganic Chemistry
- PhD in Sport Management
- PhD in Veterinary Epidemiology
- PhD in Applied Microbiology
- PhD in Genetics and Genomics
- MSc in Biomedical Sciences
- MSc in Veterinary Parasitology
- MSc in Veterinary Pathology
- MSc in Veterinary Public Health
- MSc in Athletics Coaching
- MSc in Basketball Coaching
- MSc in Exercise Physiology
- MSc in Sport Management
- MSc in Biostatistics
College of Medicine and Health Science
- MPH in Health System Management
- MSc in Emergency and Critical Care Nursing
- MSc in Medical Biochemistry
- MSc in Medical Parasitology
- MSc in Pediatrics and Child Health Nursing
- MSc in Clinical Anesthesia
College of Business and Economics
- PhD in Community Development
Institute of Technology
- PhD in Water Resources Engineering and Management (Specialization: Surface Water Hydrology, Ground Water Engineering, Irrigation Engineering and Management, Hydraulic and Hydropower Engineering, Water Supply and Sanitary Engineering)
- MSc in Hydrology and Water Resources Engineering
- MSc in Process Engineering
- MSc in Urban Planning and Development
- MSc in Water Supply and Environmental Engineering
College of Social Sciences and Humanities
- PhD in Applied Linguistics and Communication
- MA in Counselling Psychology
- MA in Educational Assessment and Evaluation
College of Education
- MA in Special Needs and Inclusive Education
Wondo Genet College of Forestry and Natural Resources
- PhD in Forest Ecology and Silviculture
- PhD in Forest Management
- PhD in Wildlife Ecology (Specialization: Ornithology, Mammalogy)