የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ/ም በተለያዩ የትምህርት መስኮች በሁለተኛ ዲግሪ እና በሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
በሦስተኛ ዲግሪ በመደበኛው ፕሮግራም በሀገር-በቀል የትብብር ዶክትሬት ፕሮግራም (Home-grown collaborative PhD program, HCPP) የሚሰጡ የስልጠና ዘርፎች፡-
- PhD in Horticulture
- PhD in Animal Biotechnology
- PhD in Agribusiness and Management
- PhD in Human Nutrition
- PhD in Aquatic Sciences, Fisheries & Aquaculture
- PhD in Management
- PhD in Agricultural Engineering
በተጨማሪም በመደበኛ ፕሮግራም በሌሎች የሶስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞችና በመደበኛ እና በእረፍት ቀናት የሁለተኛ ዲግሪ አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር የሚፈልግ ሲሆን የትምህርት መስኮቹን ዝርዝር ከዩኒቨርሲቲዉ የድረ-ገጽና ከማስታወቂያ ሰሌዳዎች መመልከት ይቻላል፡፡
የማመልከቻ መስፈርቶች
- ለሁለተኛ ዲግሪ አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ድግሪ ያለዉ/ያላት
- ለሶስተኛ ዲግሪ አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ ሁለተኛ ድግሪ ያለዉ/ያላት
- አግባብነት ካላቸዉ ተቋማት 3 የድጋፍ ደብዳቤዎች ማቅረብ የሚችል/የምትችል
- ዩኒቨርሲቲዉ የሚያወጣዉን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል
- ቀደም ሲል ከተማሩበት የትምህርት ተቋም ኦፊሺያል ትራስክሪፕት ማስላክ የሚችል/የምትችል
- አግባብነት ካላቸዉ ተቋማት የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
ማሳሰቢያ፡-
- የማመልከቻ ጊዜው እስከ ነሀሴ 10 /2013 ዓ.ም ሲሆን አመልካቾች በዩኒቨርስቲው ድህረ-ገጽ (https://portal.hu.edu.et) ላይ መመዝገቢያ ተብሎ የተዘጋጀውን ሊንክ በመከተል ONLINE መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል። ለተጨማሪ ማብራርያ የዩኒቨርስቲውን ድህረ ገጽ ይጎብኙ፡፡
ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራርና አሉሚኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት