የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ በበየነመረብ ”Online” ከሰኔ 15-20/2013 ዓ.ም ድረስ የሚከናወን ሲሆን የተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ጊዜ ሰኔ 21-22/2013 ዓ.ም መሆኑን ይገልጻል፡፡
ማሳሰቢያ፤
- ስለ ምዝገባ ሂደቱ ዝርዝር መረጃዎችን ከዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽ ፌስቡክና ቴሌግራም አካውንት ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ የሚከተሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡
1ኛ. የመስናዶና 10ኛ ክፍል ያለፋችሁበት ሰርተፍኬት
2ኛ. ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክርቢት
3ኛ. የሌሊት አልባሳት
4ኛ. 8 ጉርድ ፎቶግራፍ
5ኛ. የስፖርት ትጥቅ
ተማሪዎች በጉዞ ወቅት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል በመጠቀም እራሳቸውን ከኮቪድ በሽታ መጠበቅ እንዳለባቸው እያሳሰብን ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር እና አልሙኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት