ለሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ቅድመ ምረቃ መደበኛ እና የማታና የእረፍት ቀናት ፕሮግራም ተማሪዎች (ከ1ኛ አመትና ከዚያም በላይ ለሆናችሁ) በሙሉ

በኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠዉ የ2012 ዓ.ም የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት ለማስጀመር የመልሶ ምዝገባ የሚከናወነው ከጥር 01-03 2013 ዓ.ም መሆኑን እያሳወቅን ምዝገባውን በቀጥታ በተማሪዎች መረጃ ቋት (sis.hu.edu.et) በመጠቀም ይከናወናል።

ማሳሰብያ፡-

  1. የመደበኛ ተማሪዎች ከላይ በተጠቀሱት ቀናት በየካምፓሶቻቸው በመገኘት ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
  2. በ2012 ዓ.ም ሁለተኛ ሴሚሰተር ለ Internship ተመዝገበው የወጡ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ በቀጣይ የሚገለጽ በመሆኑ በተመደባችሁበት ቦታ እየሰራችሁ እንድትቆዩ እናሳስባለን።
  3. ለመደበኛ ተማሪዎች ትምህርት መልሶ መከፈትን በተመለከተ እና ሊደረጉ ስለሚገቡ ጥንቃቄዎች ጥር 04 ቀን 2013 ዓ.ም ገለፃ ይደረጋል፡፡
  4. ትምህርት የሚጀመረዉ ጥር 05 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  5. ተማሪዎች በጉዞ ወቅት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል በመጠቀም እራሳቸውን ከኮቪድ በሽታ መጠበቅ እንዳለባቸው እናስባለን።
  6. ከምዝገባ በፊት ወይም በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርስቲዉ የማያስተናግድ መሆኑን እያሳወቅን ስለምዝገባ ሂደቱ ዝርዝር መረጃዎችን ከዩኒቨርስቲዉ ድረ ገፅ hu.edu.et ፣Facebook እና SIS ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡

Steps on how to register online

 

ሬጅስትራርና አልሙኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et