የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና አኪኮኖሚክስ ኮሌጅ አዋዳ ካምፓስ በ2013 ዓ/ም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች በሁለተኛ ዲግሪ በእረፍት ቀን (Weekend) ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
- MA in Community Development
- MA in Cooperative Development and Leadership
- MBA in Human Resource Management
- MBA in Marketing Management
- MSc in Economics (Tracks: Developmental Economics, Environmental Economics and Financial Economics)
የማመልከቻ መስፈርቶች
- ለሁለተኛ ዲግሪ አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ድግሪ ያለዉ/ያላት
- አግባብነት ካላቸዉ ተቋማት 3 የድጋፍ ደብዳቤዎች ማቅረብ የሚችል/የምትችል
- ዩኒቨርሲቲዉ የሚያወጣዉን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል
- ቀደም ሲል ከተማሩበት የትምህርት ተቋም ኦፊሺያል ትራስክሪፕት ማስላክ የሚችል/የምትችል
- አግባብነት ካላቸዉ ተቋማት የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
ማሳሰቢያ፡-
- ምዝገባው የሚከናወነው በኦላይን ብቻ ሲሆን ምንም አይነት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ማስገባት አይቻልም፡፡
- አመልካቾች ከጥቅምት 16-22 /2013 ዓ.ም የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲው ድረገጽ (https://portal.hu.edu.et) አካውንት በመፍጠር አስፈላጊዎችን መረጃዎችን መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
- አመልካቾች የንግድ ባንክ ቁጥር 1000013481788 በመጠቀም የማመልከቻ ክፍያ 250 ብር መክፈል ይጠበቅባቸል።
- ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመልከቻ ፎርሙ በመመለስ ፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን፣ ባንክ የከፈሉበትን ደረሰኝ እና ሌሎች መረጃዎችን በማማያዝ ምዝገባዎትን ማጠናቀቅ ይኖርብዎታል፡፡
- የመግቢያ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾ ከተማሩበት ተቋም ኦፊሺያል ትራስክሪፕታቸዉ ወደ ዩንቨርሲቲዉ ሬጅስትራርና አሉምናይ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ማስላክ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በምዝገባ ወቅት ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ካልደረሰ መመዝገብ አይችሉም
- የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ጥቅምት 27/ 2013 ዓ.ም በየኮሌጆቹ ይሆናል፡፡
- የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራርና አሉሚኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት