የትምህርት ተግባራት አፈፃፀም ላይ ውይይት ተደረገ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከኤስ ኦ ኤስ ሕፃናት መንደር ፕሮግራም ሀዋሳ ጋር በመተባበር በተከናወኑ የትምህርት ተግባራት አፈፃፀም ላይ ውይይት አደረገ።

ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም በምር/ቴ/ሽ/ም/ፕ/ፅ/ቤት የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከኤስ ኦ ኤስ ሕፃናት መንደር ፕሮግራም ሀዋሳ ጋር በመተባበር በኢኮስካር (ECoS-CaR) የጋር ፕሮጀክት አማካኝነት ባለፈው አንድ ዓመት በትምህርት ላይ በተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም ዙሪያ የጋራ ውይይት አድርገዋል፡፡

የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ ፍስሐ እንደተናገሩት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢውን ሕብረተሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግርና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ባለፈው አንድ ዓመትም ከኤስ ኦ ኤስ ሕፃናት መንደር ፕሮግራም ሀዋሳ ጋር በመተባበር በኢኮስካር (ECoS-CaR) የጋር ፕሮጀክት አማካኝነት በሀዋሳ ከተማ ጨፌ ኮቴ ጀዌሳ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለሚማሩ አቅመደካማ ተማሪዎች የተለያዩ ለትምህርት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማሟላት እና ለአቅመ ደካማ ወላጆችና ተንከባካቢዎች ኑሯቸው እንዲሻሻልና ልጆቻቸውን እንዲንከባከቡ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ዳይሬክተሩ አክለው ተናግረዋል፡፡

 የኢኮስካር (ECoS-CaR) ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሰለሞን ያዕቆብ በበኩላቸው በጋራ ፕሮጀክቱ 321 አቅመ ደካማ ተማሪዎችና ወጣቶች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አስፈላጊውን የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ እየተደረጉ መሆኑን እና 125 ተንከባካቢዎችና ወላጆች ኑሯቸው እንዲሻሻልና ልጆቻቸው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እንዲያደርጉና እንዲንከባከቡ የተለያዩ ድጋፎች መደረጋቸውን ገልፀው በዚህ መድረክም ሲደረጉ የነበሩ የትምህርት ነክ ድጋፎችን ለመገምገምና በትምህርት ተግባራት አፈፃፀም ዙሪያ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን በጋራ ለመምከር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et