የመቀጠር ምጣኔ ማጎልበቻና የሙያ ማበልፀጊያ ማዕከል የሕይወት ክህሎት ስልጠና ለተማሪዎች ሰጠ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመቀጠር ምጣኔ ማጎልበቻና የሙያ ማበልፀጊያ ማዕከል የሕይወት ክህሎት ስልጠና  ታህሳስ 20 ቀን 2015 ዓ.ም  ጀምሮ ለተማሪዎች በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

የመቀጠር ምጣኔ ማጎልበቻና የሙያ ማበልፀጊያ ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ታዬ ገ/ማርያም ስልጠናውን አስመልክቶ ከዚህ በፊት ተማሪዎቻችን በዋናነት የመደበኛውን ትምህርት ብቻ በመማር የሚመረቁ ሲሆን ከተመረቁ በኃላ ስራ ከመቀጠር አንስቶ በስራ ላይም የሚያስፈልጉ ክህሎቶች ላይ ክፍተቶች እንደሚታይባቸው በጥናት ባገኘነው መሰረት ይሄንን የሕይወት ክህሎት ስልጠና ተማሪዎቻችንን ከመመረቃቸው በፊት እያሰለጠናቸው እንገኛለን ብለዋል፡፡ አክለውም ተማሪ ሰልጣኞች ቀጣሪ ድርጅቶች የሚፈልጉትን ክህሎቶች እና በስራው ዓለም የሚጠቅማቸው የተግባቦት፣ ችግር መፍቻ ዘዴዎች፣ አማራጭ መፍትሄ አፈላለግ፣ የማድመጥ እና የመሳሰሉ ክህሎቶችን በዚህ ስልጠና እንደሚሰለጥኑ ገልፀው ይህ ስልጠና የመጀመሪያው ዙር ሲሆን በቀጣይ ሳምንታቶችም በተመሳሳይ ርዕስ ስልጠናው እንደሚቀጥልና ከ300 በላይ ተማሪዎችን ለማሰልጠና መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

ማዕከሉ ስልጠናውን ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚሰጥና ስልጠናውን ከAmref Health Africa ጋር በትብብር እንዳዘጋጀው ለማወቅ ተችሏል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et