በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴ/ሽ/ም/ፅ/ቤት የ2015 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ላይና በመጀመሪያዉ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ላይ ዉይይትና ግምገማ በጥቅምት 19/2015 ዓ.ም አካሄደ።
የምርምርና ቴ/ሽ/ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ በመክፈቻዉ ላይ ሀገራችን ዕድገትና ብልፅግናን ለማምጣት በተለያዩ መስኮች ትኩረት በመስጠት እየሰራች ሲሆን ትኩረት ከተሰጣቸዉም ዘሮፎችም ትምህርት አንዱና ወሳኙ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች በትኩረት መስኮቻቸዉ መሰረት ልየታ የተደረገላቸዉ መሆኑን አዉስተዉ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲም የምርምር ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ በተነፃፃሪ ብልጫ የተለዩ የልህቀት መዕከላት፣ ደረጃቸዉን የጠበቁ ቤተ ሙከራዎች፣ ቤተ መፅሐፍት፣ የመምህራን የትምህርት ምጥጥን፣ የድህረ ምረቃ ምጥጥን፣ የምርምር ተሳትፎና ጥራት ምጥጥን፣ ቴክኖዎሎጂ ማመንጨትና ፈጠራ የመሳሰሉት መግለጫዎቻችን እንደሚሆኑ ይጠበቃል ብለዋል።
ዶ/ር ታፈሰ አክለዉም በ2014 ዓ.ም 8 መመሪያዎች ተዘጋጅተዉ ሶስቱ መፅደቃቸዉን፣ 88 አዳዲስ ምርምሮች መሰራታቸዉን፣ የምርምር ተሳትፎ መጨመሩንና የምርምር ጥራትን ለማሻሻል ስራዎች መጀመራቸዉን፣ የምርምር ዉጤቶች ታትመዉ ተደራሽ መደረጋቸዉና የላቀ አፈፃፀም ያላቸዉ ተመራማሪዎችን መገምገሚያ ስርዓት መዘርጋቱ እንዲሁም ከ12 የቴክኖሎጂ ፈጠራ ዉጤቶች ስድስቱ ፓተንት ተሰጥቷቸዉ በዩኒቨርሲቲዉ ስም ዕዉቅና መሰጠቱ የታዩ አበረታች ስራዎች መሆናቸዉን ገልፀዋል። በዚህ መድረክም በ2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን በመፈተሽ በቀጣዮቹ ጊዚያቶች ቀሪ ስራዎችን የምናቅድ ሲሆን የ2015 ዓ.ም መሪ ዕቅድም ማሻሻያ እየተደረገበት በመሆኑ ከዚህም ጋር ተያይዞ መነሳት ባለባቸዉ ነጥቦች ላይ ጊዜ ወስደን እንመክርበታለን ብለዋል።
በዕለቱም በተነሱት ነጥቦች ላይ ሰፊ ውይይት፣ ግምገማና ቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዉ ፕሮግራሙ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።