RAISE-FS ፕሮጀክት በጥራጥሬ ሰብሎች ምርትና አያያዝ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ በሚገኘው የ"RAISE-FS" ፕሮጀክት አማካኝነት የተዘጋጀውና በአኩሪ አተርና ቦለቄ ሰብሎች አመራረት፣ ድህረምርት አያያዝ፣ ስርዓተ-ጾታና ስነ-ምግብ ላይ ያተኮረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለሀዋሳ ዙሪያ አርሶአደሮችና የግብርና ባለሙያዎች መስጠት ተጀምሯል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የትብብር ፕሮጀክቶች ማስተባበሪያ ዳይሬክተር ፕ/ር መብራቱ ሙላቱ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ሲናገሩ ዩኒቨርሲቲው በርካታ የትብብር ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚንቀሳቀስ ጠቁመው አንዱም በሀዋሳ ዙሪያ የሚገኙ አርሶአደሮችን በአኩሪ አተርና የቦለቄ ሰብል ምርት እንዲሁም በዶሮ እርባታ የግብርና ዘርፎች ዙሪያ ምርምርና እገዛ እያደረገ ያለው "RAISE-FS" መሆኑን ገልፀዋል። ፕ/ር መብራቱ አክለውም መሰል ስልጠናዎች አርሶአደሩንና የአካባቢውን የግብርና ባለሙያዎች በቴክኖሎጂዎች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ በመጨበጥ በትግበራ ሂደቱ ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ስለሚያስችል ቴክኖሎጂዎችን በማላመድ ረገድ የሚገጥመውን ፈተና እንደሚቀንስ ተናግረዋል።

የ"RAISE-FS" ፕሮጀክት አስተባባሪው ዶ/ር ቴዎድሮስ አያሌው ፕሮጀክቱ የስርዓተ ምግብ ለውጥና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችን ማስተዋወቅ፣ መከታተልና የተመረጡትን ደግሞ ማላመድን ዋነኛ መንገድ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልፀው በአሁኑ ወቅት በ341 የአርሶአደር ማሳዎች ላይ እየተሞከሩ ያሉ የምርምር ግኝቶች እንደሚገኙ ገልጸዋል። በአኩሪ አተርና ቦሎቄ ሰብሎች ላይ ከአመራረትና ምርት አያያዝ ጀምሮ እስከ ገበያ ትስስርና የምግብነት ይዘት ላይ ያላቸው አስተዋጽኦ በተመለከተ ለ693 አርሶአደሮች እንዲሁም የቀበሌና ወረዳ ግብርና ባለሙያች ግንዛቤ የማስጨበጥ ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝ ዶ/ር ቴዎድሮስ አክለዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et