በሕዋ ሳይንስ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለተማሪዎች መሰጠት ተጀመረ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ጋር በመተባበር ከታህሳስ 16 - 18/2016 ዓ.ም የሚቆይ በሕዋ ሳይንስ ላይ ያተኮረ ስልጠና በዋናዉ ግቢ መስጠት ጀመረ።

የተ/ቀ/ሳ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ዙፋን በደዊ በስልጠናዉ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት በተለያዩ የሳይንስ ዘርፎች ዙርያ መሰረታዊ እዉቀትና ግንዛቤዉ ከሌላቸው ተማሪዎች ምን እንደሚያጠኑ እና ያላቸዉንም ጥቅም ካለመረዳት ባሻገር ይሄንን ተከትሎ የሚሰሩ ዘመናዊ መሳሪያዎችና መተግበሪያዎችንም በቀላሉ ሊገለገሉባቸዉና እንደማይችሉ ጠቁመው የሕዋ ሳይንስ አንዱ ዘርፍ ነዉ ብለዋል። ዲኗ አክለዉም በተፈጥሮ ከተሰጠን ፀጋ መጠቀም ለመቻል ስለዙሪያችን፣ ስለከባቢያችን እና ስለሕዋዉ ከመሰረታዊ ግንዛቤ አንስቶ መረዳት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው ይህ ስልጠና የሕዋ ሳይንስ ዕዉቀትን በመቅሰም የሕዋ ሳይንስና የኤሮስፔስ ምህንድስና ሚስጥራትን ለመገንዘብ የሚረዳ የመጀመሪያው ምዕራፍ ስልጠና እንደሚሆን በማስታወስ በዘርፉ ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎችም በርትታችሁ በመግፋትና በመማር ከግብ እንድትደርሱ ጥረት ማድረግ ይገባችኃል የሚል መልዕክታቸዉን ለሰልጣኝ ተማሪዎች አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ(ኢ.ስ.ሳ) ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ ተረፈ በበኩላቸዉ ኢ.ስ.ሳ ፍላጎት ባላቸዉ የመንግስት ተቋማት ኃላፊዎች፣ ምሁራን፣ ተመራማሪዎችና ባለሀብቶች ህብረት 47 መስራች አባላትን ይዞ የተለያዩ ሂደቶችን በማለፍ በ1996 ዓ.ም የመሰረቱት መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት እንደሆነ አስታውሰው የተመሰረተዉም በኢትዮጵያ ሳይንሳዊ ህብረተሰብ ለመፍጠር፣ የሳይንስ ባህሉ ከፍ ያለ ህብረተሰብ ለመፍጠርና ከስፔስ ሳይንስና ምህንድስና ከሚገኙ ዉጤቶች ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንድትሆን ማስቻል መሆኑን ገልፀዋል።

የኢ.ስ.ሳ ፕሮግራም ማናጀር አቶ ኪሩቤል መንበሩ የስልጠናዉን ዓላማ  አስመልክቶ እንደገለፁት ስለ ሥነፈለክ ሳይንስ፣ የሕዋ ምህንድስና እና ኤሮስፔስ ምህንድስና አጭር ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን ተማሪዎች የስፔስ ሳይንስ መሰረታዊ ዕዉቀትን የሚያገኙበት እና የ "Erasmus" ስኮላርሺፕን አስመልክቶም የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለፃ እንደሚሰጥ እንዲሁም ከተጋባዥ እንግዶች ጋር የልምድ ልዉዉጥ እንደሚደረግ ገልፀዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et