Skip to Content

በፖሊሲ ግብአት አጻጻፍ ላይ ለተመራማሪዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የም/ት/ም/ፕ /ጽ/ቤት የምርምር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በዩኒቨርሲቲው ጭብጥ-ተኮር (ቴማቲክ) የምርምር ስራዎች ላይ ለተሳተፉ  ተመራማሪዎች በፖሊሲ ግብአት አፃፃፍ (Policy Breif Development) ላይ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ተግባር ተኮር ስልጠና  ተጠናቋል።


የምርምር ጉዳይ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ፋንታሁን ይመር በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዩኒቨርሲቲው የሚሰሩ የምርምር ስራዎች በብዛትም ሆነ በይዘት ደረጃ ከፍተኛ መሻሻል እያሳዩ መምጣታቸውን ተከትሎ ምርምሮቹ ሳይንሳዊ መንገድን ተከትለው የህብረተሰቡን ችግሮች የመፍታት ኃላፊነታቸውን ከመወጣት አንፃር የመንግስት ፖሊሲዎችንና የትኩረት አቅጣጫዎችን እስከ ማሻሻል  ድረስ ተጽዕኖ ሊፈጥሩ እንደሚገባ ተናግረዋል። ስልጠናው ተመራማሪዎች የምርምር ስራዎቻቸውን አሳማኝ በሆነ መንገድ ለተቋማት የፖሊሲ ግብአት አድርገው ማቅረብና ለውጥ የማምጣት ድርሻቸውን መወጣት እንዲችሉ ከምርምር የተገኙ  ውጤቶችን ተመርኩዞ የፖሊሲ ግብአት ማዘጋጀት የሚያስችላቸውን ክህሎት የሚያላብስ መሆኑን ዳይሬከተሩ አክለዋል።



ከአሰልጣኞች አንዱ የነበሩት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ  የፖሊሲና ልማት ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተርና አንጋፋው ተመራማሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ሰመላ በበኩላቸው  ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የምርምር ስራዎችን የማከናወን ግዴታ ቢኖርባቸውም እንደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያሉ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በምርምር ስራ  እና በፖሊሲ ግብአት (policy brief) አቅርቦት ረገድ መሪ ሆነው በመውጣት ምሳሌ ሊሆኑ እንደሚገባ አስረድተዋል። ፕ/ር ተሰፋዬ ጨምረውም ተመራማሪዎች ያዘጋጁት ጥናት ሪፖርት ታይቶ እርምት ከተደረገ በኋላ ታትሞ  ለአንባቢያንና በፖሊሲ ዝግጅት ላይ ተፅዕኖ ላላቸው ውሳኔ ሰጪ አካላት የሚቀርብበት አሰራር ከጊዜ ወደ ጊዜ በተሻለ ሁኔታ እየተመቻቸ መቀጠሉን ገልጸዋል።

Share this post
Tags
Archive
Hawassa University Partners with U.S. Embassy to Host AI Impact Training for Journalists