Skip to Content

የቴማቲክ ምርምር ፕሮፖዛሎች የማጠቃለያ ግምገማ ተካሄደ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዚደንት ጽ/ቤት በምርምር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በኩል ለ2019 በጀት ዓመት የቀረቡ 12 የጭብጥ-ተኮር (ቴማቲክ) ምርምር ምክረሃሳቦች (ፕሮፖዛሎችን) የመጨረሻ ግምገማ በማካሄድ ወደ ትግበራ የሚገቡበትን በጀት ለመልቀቅ ያዘጋጀው መርሐ-ግብር ተካሂዷል።

መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው የምር/ትብ/ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ታፈሰ ማቴዎስ እንደተናገሩት በዩኒቨርሲቲው የሚካሄዱ ምርምሮች ለህብረተሰቡ ችግሮች መፍትሔ የሚሰጡና ለሀገር ዕድገት ጉልህ አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ መሆን አንዳለባቸው ገልጸው በዚህ ረገድ ከዓመት ወደ ዓመት በዩኒቨርሲቲው እየተሰሩ የሚገኙ ምርምሮች የተሻለ አፈጻጸም እያመጡ መሆኑን መስክረዋል። ዶ/ር ታፈሰ አክለውም የምርምር ግምገማ ሥርዓቱ 50% ግልጽ ያልሆነ የባልደረባ ግምገማ (blind peer review) እና 50% በባለሙያዎች ፓነል የሚደረግ ግልጽ ግምገማ (open defence) ያካተተ መሆኑን በመግለጽ በዚህ ሂደት ውስጥ የሚሳተፉ ገምጋሚዎች እውነተኛ (objective) እና ሥነ-ምግባራዊ በሆነ መልኩ የግምገማ ስራውን እንዲያከናውኑ አበረታተዋል።


የምርምር ጉዳዮች ዳይሬክተር ፕ/ር ፉንታ ይመር በበኩላቸው በ2019 ዓ.ም በተደረገው ጥሪ መሠረት መስፈርቱን ያሟሉ 12 የቴማቲክ ምርምሮች ለዚህ የማጠቃለያ ግምገማ መቅረባቸውን የገለጹ ሲሆን ምርምሮቹ በሳይንሳዊ፣ ሙያዊና ስነ-ምግባራዊ መለኪያዎች እንደሚገመገሙ በተጨማሪነትም የፖሊሲ ገለጻ የማዘጋጀታቸው፣ የያዙት የተለየ ግኝት፣ በህብረተሰቡ ኑሮና በኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ የሚያሳድሩት አዎንታዊ ተጽዕኖ በጥብቅ ይታያል ብለዋል። እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ በሁለት ዙር በተካሄደው ግምገማ ከ70% በላይ ውጤት ላስመዘገቡት የቴማቲክ ምርምር ፕሮፖዛሎች ወደ ትግበራ የሚገቡበት የምርምር ማስኬጃ በጀት የሚለቀቅላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

Share this post
Tags
Archive
Hawassa University and JLU Giessen Explore New Frontiers in Joint Research and Student Exchange