በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የምርምር ቀንን አከበረ

በዓለማችን እና በሀገራችን አስከፊው የኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ ወረርሽኙን በተመለከተ በርካታ የምርምር ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በኩል በተመራማሪዎች የተሰሩ አስር የምርምር ውጤቶች የካቲት 12 ቀን 2013 ዓ.ም ለባለድርሻ አካላት ለውይይት ቀርበዋል፡፡

አቶ አለሙ ጣሚሶ (ረ/ፕ) የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  የፕሮግራሙ ዓላማ የኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ አስር ምርምሮችን መሰራታቸውንና የእነዚህንም  የምርምር ውጤቶች ለማህበረሰቡ አቅርቦ ውይይት  ማድረግና የምርምር ቀን ማክበር በማስፈለጉ ይህ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ብልጫ ላስመዘገቡ መምህራንና ተመራማሪዎች የእውቅና ሽልማት ለመስጠት መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር መሳይ ሀይሉ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አንዱ ተልዕኮ የምርምር ውጤቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ እና ተግባራዊ ማድረግ መሆኑን ገልጸው በዕለቱ የቀረቡት የምርምር ስራዎች ለአለም ጤና ስጋት በሆነው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ላይ በመሆኑ ህብረተሰቡ ስለ ወረርሽኙ ያለውን ግንዛቤ ለመረዳትና ለማሳደግ፣ ለሳይንሱ ማህበረሰብ ተጨማሪ ምርምሮችን እንዲሰሩ፣ የተሰሩ ስራዎች ምን ያህል ውጤታማ እንደሆኑ ለመገምገም፣ ለመማር ማስተማሩ ምን አስተዋፅዖ እንዳበረከቱ እንዲሁም ተጨማሪ መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች አቅጣጫ ለማስቀመጥ ይረዳል ብለዋል፡፡

በዕለቱም የተሰሩት የምርምር ውጤቶች ቀርበው ውይይት ከተደረገ በኃላ በምርምርና  ማህበረሰብ አገልግሎት ብልጫ ላስመዘገቡ መምህራን እና ተመራማሪዎች የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸው ፕሮግራሙ መጠናቀቁ ታውቋል፡፡

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 887 1511 
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et