በመረጃ አያያዝ ዕቅድና የአፈጻጸም ሪፖርት አዘገጃጀት ላይ ለባለሙያዎች ሥልጠና ተሰጠ

የሥልጠናውን  መድረክ በወንዶገነት ደ/ተ/ሀ/ኮሌጅ ያዘጋጀው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕላንና ተቋማዊ ለውጥ ዳይሬክቶሬት ሲሆን በመረጃ ፍሰት፣ በስትራቴጂካዊ ዕቅድ አዘገጃጀትና የአፈጻጸም ሪፖርት አቀራረብ ላይ የሚታየውን ክፍተት ለማጥበብ

ብሎም የተሻሻሉ አቀራረቦች ላይ መረጃዏችን በማካፈል የባለሙያዎችን ዕውቀት ከፍ ለማድረግ የታቀደ መሆኑን የዳይሬክቶሬቱ ዳይረክተር አቶ ሙሉጌታ በመክፈቻ ንግግራቸው ጠቁመዋል።

በስልጠናው ላይ በዘርፉ ባለሙያ አቶ ሰርካዲስ አማካይነት የመረጃ አያያዝና ፍሰት ጉዳይ ተነስቶ ውጤታማ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በተደረገው ውይይት እስካሁን የነበረው ማኑዋል ሲስተም በመሆኑ ለቀልጣፋ አገልግሎት ይህን ሁኔታ ማሻሻልና ማዘመን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በበለጸገው ሶፍትዌር በመጠቀም መረጃን በአግባቡ ለመያዝና በፍጥነት ለማሰራጨት የሚረዳ የቡድን ኢሜይል ተከፍቶ ሠልጣኞቹ ማረጋገጥ እንዲችሉ የአይሲቲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እሱባለው ገ/ማሪያም በዕለቱ ከፍተኛ እገዛ አድርገዋል፡፡  

በመጨረሻም ዘመናዊ ስልቶችን በመጠቀም መረጃን መያዝ፣ በአግባቡ ማቀድና በጊዜና በጥራት ሪፖርት ማድረግ ካሁኑ ትውልድ የሚጠበቅ በመሆኑ ከዚህ አኳያ ስልጠናው ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸው መድረኩን ያጠቃለሉት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ አየለ አዳቶ ናቸው፡፡ አቶ አየለ አክለው በቂ አቅም እስኪፈጠር ይህ ሥልጠና ተጠናክሮ መቀጠልና ከየኮሌጆቹና ተቋሞቹ ሀላፊዎችና የዕቅድ ባለሙያዎች ብሎም እያንዳንዱ ግለሰብ ተደራሽ መደረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች በየኮሌጆቹ ወይም በየካምፓሶቹ በመረጃ አያያዝ፣ በዕቅድና ሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘገጃጀት ቀጥተኛ ድርሻ ያላቸውና ሌሎችም የሥራ ክፍሎች አመራሮች እንዲሁም የም/ፕሬዝዳንቶች ጽ/ቤት ልዩ ረዳቶች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 887 1511 
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et