የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎችን አስመረቀ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ.ም ሲያስተምራቸው የነበሩትን የመጀመሪያ፣ የሁለተኛ እና የሶስተኛ ድግሪ 4780 ተመራቂ ተማሪዎችን በነሐሴ 23/2012ዓ.ም እንዳስመረቀ የሚታወቅ ሲሆን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የኮቪድ-19

ወረርሽኝን እየተከላከሉ ከፍተኛ ትምህርትና ስልጠናን ለማስቀጠል ያወጣውን መመርያ ተግባራዊ በማድረግ 6263 ተማሪዎችን ለሁለተኛ ጊዜ በታህሳስ 24/2013ዓ.ም አስመረቀ፡፡

ዶ/ር አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በዕለቱ ተገኝተው ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ 10 ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ የመሆን ራዕይ አቦ በመሥራት ላይ እንዳለ ገልጸው ዩኒቨርሲቲው በ8 ኮሌጆች እና በ3 ኢንስቲትውቶች 102 የመጀመሪያ ድግሪ፣ 122 የሁለተኛ ድግሪ እና 21 የሶስተኛ ድግሪ ፕሮግራሞችን በመክፈት ከ43800 በላይ ተማሪዎችን በመደበኛና በተከታታይ ትምህርት በሰባት ካምፓሶች እያስተማረ የቆየ ሲሆን ያልተጠበቀው የኮሮና ወረርሽኝ በመከሰቱ ትምህርት ለወራቶች ተቋርጦ ቢቆይም አስቸጋሪውን ጊዜ በመቋቋምና ትምህርትንም መልሶ በመክፈት የምረቃው ጊዜ ቢዘገይም  ይህንን አስቸጋሪ ወቅት አልፈው ለዛሬዋ ቀን በመድረሳቸው ተመራቂ ተማሪዎችን እና የተመራቂ ቤተሰቦችን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

የዕለቱ የክብር እንግዳ ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር በዕለቱ ተገኝተው በአለምና በሀገራችን ላይ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ብዙ ጫና ባደረሰበት በዚህ ወቅት የሚቻለውን ሁሉ ጥረት አድርጋችሁ ለዚህ ዕለት በመብቃታችሁ እጅጉን የሚያስመሰግናችሁ ነው ያሉ ሲሆን ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲም በዚህ ጫና ወቅት የመማር ማስተማር፣ ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ሥራውን አጠናክሮ መቀጠሉ የአመራሩን እና የሠራተኞቹን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እና የሚያስመሰግን ተግባር ነው ብለዋል፡፡

ርዕሰ-መስተዳድሩ አክለውም ዜጎች ሥራ ሠርተው ራስን፣ ቤተሰብንና ሀገርን ሊጠቅሙ የሚችሉት ሰላምና ሀገራዊ አንድነት ሲኖር ሲሆን ለሁላችንም የሚበቃ ሀብት መፍጠሪያ መንገዱ የሰውን አቅም እውቀትና ክህሎቱ ከሚፈቅድለት ዝንባሌው ጋር ማገናኘት ሲቻል በመሆኑ ሰው ተዘዋውሮና ተባብሮ መክሊቱን እንዲያገኝ መሰረቱ ሰላም ነው፡፡ ሰላም በሀገራችን እንዲሰፍን በያለንበት የድርሻችንን መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 887 1511 
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et